ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የቻይና ህዝባዊ ሪፑብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይን ዛሬ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=yJGl1PI8qiY
ሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የጠበቀ የረጅም ጊዜ ግንኙነትና ቻይና ለኢትዮጵያ የምታደርገውን አስተዋጽኦ ያነሱት ጠ/ሚር ዐቢይ ከመሰረተ ልማት እድገት በተጨማሪ አዲሱ የትብብር አድማስ የቴክኖሎጂ እድገት ላይ ሊያተኩር ይገባል ብለዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዋንግ ይም በበኩላቸው በኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ወራት እየተካሄዱ ያሉ ስኬታማ የለውጥና ማሻሻያ ሥራዎችን አድንቀዋል፡፡ ኢትዮጵያ በትክክለኛ አቅጣጫ ላይ ትገኛለች ያሉት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አገራቸው ቻይና የኢትዮጵያን የልማት እንቅስቃሴዎችና አዳዲስ የልማት ገፅታዎች ዙሪያ ለመተባበር ፍቃደኝነቷን ገልፀዋል ሲል የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት አስታውቋል::