ከመስከረም ወር አጋማሽ ጀምሮ በታጣቂዎች ተዘግቶ የነበረው የካማሸ ዞን መንገድ መከፈቱን የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል አስታወቀ።
https://www.youtube.com/watch?v=yJGl1PI8qiY
በቤንሻጉል ጉሙዝ እና በኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ ዞንና ወረዳዎች የተከሰተውን ግጭት ለማስቆም የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ተጨባጭ የሆኑ ውጤቶችን ማስመዝገቡን ማስታወቁን በትናንትናው ዕለት መዘገባችን ይታወሳል::
ኮማንድ ፖስቱ እንዳለው በአካብባቢው ግጭቱን ሲመሩ የነበሩ የታጠቁ ፀረ-ሰላም ኃይሎች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን እንዲሰጡ ይህን ያልተቀበሉ ኃይሎች ላይ ደግሞ ከገቡበት ገብቶ የማያዳግም የኃይል እርምጃ በመውሰድ አበረታች ውጤቶች ተመዝግቧል፤
– በተሳሳተ መንገድ ከጥፋት ሃይል ጎን ተሰልፈው መንገድ ሲዘጉ፣ ህብረተሰብን ሲያንገላቱ ብሎም የግድያ፣ የዘረፋ እና ከቀያቸው የማፈናቀል ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ የጥፋት ሃይሎች በቁጥጥር ስር እንዲዉሉ እንዲሁም ሲጠቀሙበት የነበሩ በርካታ መሳሪያዎችና በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በቁጥጥር ስር ውሏል፤