ከአላሙዲ የተቀማው መሬት የሕዝብ መናፈሻ ፓርክ ሊሆን ነው

November 24, 2018

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ ከአላሙዲ የተነጠቁት መሬቶች መናፈሻ አንደሚሆኑ አስታወቁ:: ከንቲባው በትዊተር ገጻቸው ሲናገሩ <<አስተዳደሩ በከተማው የሚታየው የአረንጓዴ መስህብ ቦታዎች እጥረት እና የወጣቶች ጊዜ ማሳለፊያ ቦታዎችን ችግር ለመቅረፍ በከተማዋ እንብርት(ማዘጋጃ ቤቱ ፊት-ለፊት) ለረጅም ግዜ ያለአገልግሎት የቆየውን ቦታ እና ለከፊል ሸራተን ማስፋፍያ በሚል ተይዞ የነበረውን ቦታ ለህዝብ መዝናኛ የሚውል የአረንጓዴ ስፍራ ለማድረግ ወስኗል፡፡>> ብለዋል:: ጨምረውም <<አረንጓዴ መናፈሻዎቹ አገልግሎት መስጠት ሲጀምሩ ለከተማዋ ተጨማሪ ውበት፤ የካርበን ልቀትን የሚቀንሱ አረንጓዴ ስፍራዎች እንዲሁም ለወጣቶች የስራ እድልን የሚያስገኙ ይሆናሉ፡፡>> ሲሉ አስረድተዋል::

በከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ የሚመራው አዲሱ የከተማዋ አስተዳደር አዲስ አበባን አንደስያሜዋ ውብ አና ለነዋሪዎቿ የተመቸች ማድረግን ቀዳሚ ስራው አድርጎ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ሲሆን ከዚህ ጋር የተያያዙ እቅዶችንም በቅርቡ ለህዝቡ ይፋ እንደሚያደርግ ኢንጅንር ታከለ ተናግረዋል።
አላሙዲ ለረዥም ጊዜ አጥሮት የቆየው ይህ ስፍራ አላሙዲ ከማጠሩ በፊት የከተማው ወጣቶች ኳስ መጫወቻና የተለያዩ ስፖርቶች ማከናወኛ ነበር::
https://www.youtube.com/watch?v=ibs_Mi6_X_s

Previous Story

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ

Next Story

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለመቀሌ ውሀ አገልግሎት አቅርቦት ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ይሆን ዘንድ ከቻይና ኤክስፖርት ኢምፖርት ባንክ የተገደረገውን የብድር ስምምነት ተቀበለ

Go toTop