35 በሚሊዮን ብር የሚቆጠሩ ንግድ ድርጅቶችን የሚያንቀሳቅሱ ነጋዴዎች ዛሬ በቁጥጥር ስር ዋሉ:: ነጋዴዎቹ በዛሬው ዕለት ከየቦታው ተለቃቅመው የታሰሩት የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት 10 ቀናት ባደረገው የክትትል ስራ ያለደረሰኝ ግብይት ሲፈጽሙ የነበሩ ናቸው በሚል ነው::
በሚሊየን የሚቆጠር ብር የሆነ ተቋማትን የሚያንቀሳቅሱት እነዚሁ ዛሬ በቁጥጥር ስር የዋሉት ነጋዴዎች ሰኞ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል”:: የገቢዎች ሚኒስትር ዛሬ በሰጠው መግለጫ “በነዚህ ሚሊዮን ብሮችን በሚያንቀስቅሱት ተቋማቱ ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እና ተግባሩ የወንጀል ድርጊትም በመሆኑ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን እና 35 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን” ይፋ አድርጓል::
ዛሬ በሕገወጥ መንገድ ካለደረሰኝ በመሸጥ መንግስት ሊያገኝ የሚገባውን ጥቅም በማስቀረት በሌብነት ወንጀክ ተጠርጥረው የታሰሩት ባለሃብቶች የሚያንቀሳቅሷቸው ተቋማት ዝርዝር:
1. ምስራቅ ሃ/የተ/የግ/ማ/ ተክለሃይማኖት ቅርንጫፍ/
2. ምስራቅ ሃ/የተ/የግ/ማ/ አጎና አካባቢ ቅርንጫፍ
3. ምስራቅ ሃ/የተ/የግ/ማ/ ጎተራ አካባቢ ቅርንጫፍ
4. ምስራቅ ሃ/የተ/የግ/ማ/ ደንበል ቀርንጫፍ
5. ቬልቬት የውበትና ጽዳት ሃ/የተ/የግ/ማ/
6. ባዝራ ፈረስ ሌዘር ላኪ ሃ/የተ/የግ/ማ/
7. ቢኤምኤች አጠቃላይ ንግድ
8. በላክ ትሬዲንግ ሃ/የተ/የግ/ማ/
9. ድናሪም ትሬዲንግ ሃ/የተ/የግ/ማ/
10. አፍደል ሃ/የተ/የግ/ማ/
11. ደሚር ትሬዲንግ ሃ/የተ/የግ/ማ/
12. ሞጀግ ሃ/የተ/የግ/ማ/
13. ፋሙ ኤሌክትሪካል ዎርክስ
14. አስተኑ ጄኔራል ትሬዲንግ
15. ዕድላዊት ስቴሽነሪ
16. ጆቢራ ካፌ ሃ/የተ/የግ/ማ/
17. ኪው ቲ ትሬዲንግ
18. አሰብ ሆቴል ናቸው::
ዘ-ሐበሻ ከዚህ ቀደም እንደዚህ ባሉ ነጋዴዎች ላይ የገቢዎች ሚኒስትርና የፌዴራል ፖሊስ ምርመራ እያካሄዱ መሆኑን መዘገቡ ይታወሳል::
https://www.youtube.com/watch?v=wcjYZaYCiUM&t=245s