Español

The title is "Le Bon Usage".

ሜጀር ጀነራል ክንፈ ወደ ሱዳን ሊያመልጡ ሲሉ ሁመራ ላይ ተያዙ

November 13, 2018

የቀድሞ የብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ከቀድሞ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ዋና ዳሬክተር ከነበሩt ሜጀር ጀነራል ተክለብርሀን ወልደአረጋይ ጋር በመሆን ከሃገር ሊሸሹ ሲሉ ተያዙ:: ጄነራሎቹ ትናንት ከሰዐት በኅላ፣ በወልቃይት አዲረመጥ ከተማ ወደ ባዕከር ሁመራ ማምራታቸውን ሕብረተሰቡ ለወታደሮች ጥቆማ እንደሰጠ ተሰምቷል። ወደ ሱዳን ለማምለጥ እየሄድይ ባለበት ወቅት በተደረገባቸው ክትትል ሁመራ ላይ የተያዙት በትግራይ ልዩ ፖሊስ እና በመከላከያ ሰራዊቱና ከአዲስ አበባ በተላኩ ደህንነቶች ትብብር መሆኑ ተገልጿል::

በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ጀነራል ክንፈ ወደ ሱዳን ለማምለጥ ሲሞክሩ እንዴት እንደተያዙ ነው::

በሁመራ ባካር በተባለ አካባቢ ለማምለጥ ሲሞክሩ የተያዙት ሜጀር ጀነራል ክንፈ በሌብነት ወንጀል ተጠርጥረው ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ መጥተዋል::
ከጀነራል ክንፈ ጋር አብረው የተከሰሱት እነ ብርጋዲየር ጄኔራል ጠና ኩርዲንን ጨምሮ 28 የሜቴክ ሰራተኞች ትናንት ፍርድ ቤት በቀረቡበት ወቅት ከቀረቡባቸው የሌበነት ወንጀል ክሶች መካከል የስኳር ገንዘብን ያለአግባብ በመጠቀም፣ የህዳሴ ግድብና የያዩ ማዳበሪያ ፕሮጀክቶች ላይ ህግን ያልተከተለ ግዢ በመፈፀም የሚሉ እንደተካተቱበት ሰምተናል::

ዘ-ሐበሻ ከቀናት በፊት በፍርድ ቤት የሚከፈተው የሌብነት ወንጀል ክስ በ ነጀነራል ክንፈ ዳኘው ተብሎ እንደሚጠራና ክንፈ እንዳልተያዙ የፖሊስ ምንጮቹን ጠቅሶ ነበር:: አሁን የጀነራሉን መያዝ ተከትሎ በቀጣይ የክሱ ፋይል መጠሪያ በርሳቸው ስም ይሆናል::

ይህ በ እንዲህ እንዳለ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በሌብነት ተጠርጥረው እስካሁን የታሰሩትን የ27 ከፍተኛ የጦር መኮንኖችን እና ተባባሪዎቻቸውን ስም ዝርዝር ይፋ አደረገ::
ዝርዝሩ እንደሚከተለው ይቀርባል
1. ብርጋዴር ጄኔራል ጠና ቁርንዴ ኢጄታ – በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የማርኬቲንግ ኃላፊ
2. ብርጋዴር ጄኔራል ብርሃ በየነ – በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የኮርፖሬት ኦዲትና ኢንስፔክሽን ኃላፊ
3. ብርጋዴር ጄኔራል ጥጋቡ ፈትላ መረሳ – በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የኮርፖሬት ሎጂስቲክስና ሰፕላይ ኃላፊ
4. ብርጋዴር ጀኔራል ሃድጉ ገብረጊወርጊስ ገብረስላሴ – በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የኮርፖሬት ኒው ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ኃላፊ
5. ኮሎኔል ሸጋው ሙሉጌታ ተስፋሁን – በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የወታደራዊ ምርቶች ኦፕሬሽን ኃላፊ
6. ኮሎኔል ሙሉ ወልደገብርዔል ገብረእግዛብሄር – በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የኒው ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ኃላፊ የነበሩ
7. ኮሎኔል ዙፋን በርሄ ይህደግላ – የመከላከያ ጤና ኮሌጅ ሰራተኛ
8. ሌተናል ኮሎኔል አስምረት ኪዳኔ አብርሃ – የጋፋት አርማመንት ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ተወካይ ኃላፊ የነበሩ
9. ኮሎኔል አለሙ ሽመልስ ብርሃን – በብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን በኮርፖሬት ሎጂስቲክስና ሰፕላይ የትራንስፖርት ኃላፊ
10. ኮሎኔል ያሬድ ሃይሉ – በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በኮርፖሬት ኒው ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት የፕሮጀክት ኃላፊ
11. ኮሎኔል ተከስተ ሀይለማሪያም አድሃኑ – በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የኒው ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ኃላፊ የነበሩ
12. ኮሎኔል አዜብ ታደሰ – በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በኮርፖሬት ማርኬቲንግ የሽያጭ ኃላፊ
13. ሻለቃ ሰመረ ሀይሌ ሀጎስ – በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በደጀን አቪዬሽን የኢንዱስትሪ ኦፕሬሽን ኃላፊ
14. ሻምበል ይኩኖአምላክ ተስፋዬ – በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በኮርፖሬት ማርኬቲንግና ሽያጭ የፕሮሞሽን ኃላፊ
15. ኮሎኔል ደሴ ዘለቀ ብርሃን – በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የአዳማ እርሻ ስራዎች ኢንዱስትሪ ስራ አስኪያጅ
16. ሌተናል ኮሎኔል ሰለሞን በርሄ – በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በብረታ ብረት ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ የፋይናንስ ኃላፊ
17. ሻለቃ ይርጋ አብርሃ – በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በህብረት ማሽን ቢዩልዲንግ ኢንዱስትሪ የፋይናንስ ኃላፊ
18. ኮሎኔል ግርማይ ታረቀኝ – በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በኮርፖሬት ሎጂስቲክስና ሰፕላይ የንብረት አስተዳደር ኃላፊ
19. ሻምበል ገብረስላሴ ገብረጊዮርጊስ – በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የኮርፖሬት ትራንስፎርሜሽን የአቅም ግንባታ ማዕከል ኃላፊ
20. ሻምበል ሰለሞን አብርሃ – በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በኮርፖሬት ትራንስፎርሜሽን የስልጠና ኃላፊ
21. ሻለቃ ጌታቸው ገብረ ስላሴ – በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የደን ምንጣሮ ክትትል ኃላፊ
22. ሌተናል ኮሎኔል ይሰሃቅ ሀይለማሪያም አድሃኖም – በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በኮርፖሬት ኮሜርሻልና ሲቪል ምርቶች ኦፕሬሽን የፕላኒንግና ኮንትሮል ኃላፊ
23. ሻለቃ ክንደያ ግርማይ – በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች የፋይናንስ ኃላፊ
24. ሌተናል ኮሎኔል አዳነ አገርነው – በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በኮርፖሬት ሎጂስቲክስና ሰፕላይ የንብረት ክፍል ኃላፊ
25. ሻለቃ ጌታቸው አጽብሃ – በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ኢንፍራስትራክችርና ኮርፖሬሽን ማሽነሪ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኦፕሬሽን ኃላፊ
26. ቸርነት ዳና – የዋይ ቲ ኦ ኩባንያ ባለቤትና ከብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን አመራሮች ጋር የጥቅም ትስስር የነበራቸው ደላላ
27. አያልነሽ መኮንን አራጌ – ማስረጃ ልታጠፋ ስትል በቁጥጥር ስር የዋለች
https://www.youtube.com/watch?v=Kiw-PSSXvLY

Previous Story

ወይዘሮ ብርቱካን ሚደቅሳ የህግ የበላይነት ከሌለ ሁሉም እያዘዘ የሚኖርበት ስርአት ይፈጠራል አሉ

Next Story

በምእራብ በግጭት ምክንያት ኦሮሚያ 26 ትምህርት ቤቶች ተዘጉ

Zehabesha | Ethiopian Latest News, Top Analysis & Best Articles <h1 style="text-align:center">tHE HABESHA Ethiopian Reliable News Source – Truth Will Win</h1><title> <title><h2 style="text-align:left">Get the Best Scholarly Articles and Analysis on ZeHabesha</h2><title> <title><h3 style="text-align:right">Zehabesha Ethiopian News</h3><title> <title><h4 style="text-align:justify">Ethiopian Lates News</h4><title> <meta name="keywords" content="Ethiopian News, Ethiopia News, Ethiopian News Today, Top Stories, The Habesha, Latest News, Ethiopia, Breaking News, zehabesha, zehabesha Amharic News, The Habesha News, Headlines, borkena. bbc amharic, repoter, mereja, Ethiopian News provider"> <!-- Google Tag Manager --> <script>(function(w,d,s,l,i){w[l]=w[l]||[];w[l].push({'gtm.start': new Date().getTime(),event:'gtm.js'});var f=d.getElementsByTagName(s)[0], j=d.createElement(s),dl=l!='dataLayer'?'&l='+l:'';j.async=true;j.src= 'https://www.googletagmanager.com/gtm.js?id='+i+dl;f.parentNode.insertBefore(j,f); })(window,document,'script','dataLayer','GTM-5WDL6STX');</script> <!-- End Google Tag Manager --> <!-- Google tag (gtag.js) --> <script async src="https://www.googletagmanager.com/gtag/js?id=G-W9E3TWE2TL"></script> <script> window.dataLayer = window.dataLayer || []; function gtag(){dataLayer.push(arguments);} gtag('js', new Date()); gtag('config', 'G-W9E3TWE2TL'); </script> <meta name="msvalidate.01" content="4781C31A916C7AB883D8AF1F4F3BFC49" /> <link rel="icon" href="/path/to/favicon.ico"> <link rel="icon" type="image/png" href="/thehabesha.com/favicon-96x96.png" sizes="96x96" /> <link rel="icon" type="image/svg+xml" href="/thehabesha.com/favicon.svg" /> <link rel="shortcut icon" href="/thehabesha.com/favicon.ico" /> <link rel="apple-touch-icon" sizes="180x180" href="/thehabesha.com/apple-touch-icon.png" /> <link rel="manifest" href="/thehabesha.com/site.webmanifest" /> <meta name="seobility" content="48b995a16caf3ab9d546a000c18b65d3"> <main> <!-- Main content of your page goes here --> </main> <script type="text/javascript" src="//cdn.rlets.com/capture_configs/d2b/aac/e54/1fc4f7ea32cf1e1d818a0f2.js" async="async"></script> <script async src="https://www.googletagmanager.com/gtag/js?id=TAG_ID"></script> <script src="https://www.googleoptimize.com/optimize.js?id=OPT-M8Z33GL"></script> <meta name="google-site-verification" content="Lf_65x5pXGn-W1TA8CsfJi-53aAyIKdfVyM_QkwpvgY" /> <head> <title>Ethiopian Latest News: Top Analysis and the best Articles<title> <script defer data-domain="thehabesha.com/mEUHSv" src="https://api.publytics.net/js/script.manual.min.js"></script> <script> window.publytics = window.publytics || function() { (window.publytics.q = window.publytics.q || []).push(arguments) }; publytics('pageview'); </script> <!-- Google tag (gtag.js) --> <script async src="https://www.googletagmanager.com/gtag/js?id=UA-215686007-9"></script> <script> window.dataLayer = window.dataLayer || []; function gtag(){dataLayer.push(arguments);} gtag('js', new Date()); gtag('config', 'UA-215686007-9'); </script> <script async src="https://pagead2.googlesyndication.com/pagead/js/adsbygoogle.js?client=ca-pub-9091845805741569" crossorigin="anonymous"></script> <script async custom-element="amp-ad" src="https://cdn.ampproject.org/v0/amp-ad-0.1.js"></script> <title>Zehabesha Ethiopian Reliable News Source – Truth Will Win