የአዲስ አበባ ወጣቶች ክስ ወደሽብርተኝነት ተቀየረ

November 1, 2018

(ዘ-ሐበሻ) የኦነግ አቀባበልን ተከትሎ በቡራዩና አካባቢው የተፈጠረውን ችግር ምክንያት በማድረግ ከታፈሱት የአዲስ አበባ ወጣቶች አብዛኛዎቹ ቢለቀቁም ማስረጃ አግኝቼባቸዋለሁ ያላቸው 83 ያህሉ በፍርድ ቤት ክሳቸው እየታየ መሆኑ ይታወቃል፡፡ እነዚህ ወጣቶች በአራዳ ፍርድ ቤት ጉዳያቸው በጊዜ ቀጠሮ ሲታይ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን ከትላንት በስቲያ ምክሰኞ ልደታ በሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ከፍተኛ ውዝግብ አስነስቷል፡፡ በዚህ የተነሳም በታሳሪ ቤተሰቦችና በፀጥታ አካላት መሃከል ግጭት ተቀስቅሶ እንደነበር ምንጮቻችን ገልፀውልናል፡፡

እንደነዚህ ምንጮች ወጣቶቹ ቀደም ሲል አራዳ ፍርድ ቤት ይቀርቡ የነበረው የተጠረጠሩበት ወንጀል ነፍስ ግድያና አካል ማጉደል ስለነበረ ነው፡፡ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ግን ክሳቸው ወደሽብርተኝነት ተቀይሮባቸዋል፡፡ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የሽብርን ወንጀል የማየት ስልጣን የለኝም በሚል ነው ልደታ ወደሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት መዝገባቸው የተዘዋወረው፡፡ በሽብር የተጠረጠረ ሰው የዋስትና መብት የሚከለከል መሆኑ ይታወቃል፡፡

ጃዋር መሃመድ የኦነግን አቀባበል ተከትሎ በሳሪስና መርካቶ 43 ሰዎች ተገደለዋል::” ብሎ መናገሩ ይታወሳል:: የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽን ኮምሽነር ሜጀር ጀነራል ደግፌ በዲ በበኩላቸው “በኦነግ አቀባበልን ተከትሎም በአዲስ አበባ 28 ሰዎች ሞተዋል:: ከእነዚህም ውስጥ በፀጥታ ኃይል የተገደሉ 7 ብቻ ናቸው:” ማለታቸው ይታወሳል::

https://www.youtube.com/watch?v=NaLy5pGAFTc

Previous Story

ፓርላማው በሙስና/ሌብነት የተጠረጠሩ አባላቱን ያለመከሰስ መብት ሊያነሳ ነው

Next Story

የግብጹ ባለስልጣን የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ በሚቀጥሉት አመታት እንደሚፈርስ ተናገሩ

Go toTop