ኮለኔል አያናው መስፍን ቤተመንግስት ከሄዱት የወታደሮች ጀርባ አሉበት ተብለው ተጠርጥረው ታሰሩ

October 17, 2018

ከወራት በፊት ከአጋዚ ጦር ጋር የሚመሳሰል ‘ማበል ግብረሃይል’ የተባለ በዶ/ር ዓብይ አህመድ አማካኝነት እንዲቋቋም የተደረገ ሲሆን ከዚህ ከማበል ግብረሃይል አንዱ ሻምበል ወደ ቤተመንግስት ከነጠመንጃው መሄዱ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው የውስጥ መረጃ ይጠቁማል::

ከማበል ግብረሃይል በኮለኔል አያናው መስፍን ከበላይ ሆኖ የሚያዘውና ማዕረጋቸው ለጊዜው ማዕረጋቸው ያልተገለጸ ሞሲሳ እና በምክትሉ ፈቃዱ የሚመራው ሻምበል ጦር ወደ ቤተመንግስት በመሄዱ ከበስተጀርባው ያለው የደመወዝ ጥያቄ ሳይሆን ሌላ ነው በሚል ሦስቱም የክፍተኛ የጦር መኮንኖች ተጠርጥረው መታሰራቸውን የመከላከያ ምንጮች ገልጸዋል::

በቡራዩ የተከሰተውን ሁኔታ ለማርገብ ከአዋሳ የመጡት እነዚሁ ሞሲሳ እና ፈቃዱ የሚመሩት ሻምበል ጉዳይ አሁንም መነጋገሪያነቱ የቀጠለ ሲሆን በወታደሮቹ መሰረታዊ የደመወዝ ጥያቄ ጀርባ ሌሎች የተሴሩ ነገሮች ናቸው በሚል መከላከያው አሁንም እየታመሰ መሆኑ ታውቋል::

ለጊዜው የሶስቱ ከፍተኛ ጦር መኮንኖች ስም የመታሰራቸው ስም ይፋ ይሁን እንጂ በርካታ ሃላፊዎች እየታሰሩና
እየተገመገሙ ይገኛሉ::
_
https://www.youtube.com/watch?v=d1wWzuTMu2s

Previous Story

አሥር ሴቶች የተካተቱበት የጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲሱ ካቢኔ በፓርላማ ፀደቀ | በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት መከላከያ ሚ/ር መረጠች

Next Story

ሰባተኛው ንጉሥ ጉድ አፈላ! – ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

Go toTop