የኢትዮጵያ እስልምና እና የዑለማዎች ምክር ቤት ይፍረሱ በሚል የቀረበው አቤቱታ ውድቅ ከተደረገ በኋላ ፤ በድጋሚ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት እንደሚቀርብ ኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ ጥቅምት 6 ቀን 2006 ዓ.ም.ባወጣው እትሙ አስነብቧል፡፡
የታሰሩት የኢትዮጵያ ሙስሊም ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ጠበቃ ተማም አባ ቡልጉ እንደተናገሩት፤ የተጀመረው ክስ ለመስከረም 27 ቀን 2006 ዓ.ም. ድጋሚ ያስቀርባል አያስቀርብም የሚለውን ለማየት እንደነበር ተናግረው ፤ ጉዳዩ ተብራርቶ በመቅረቡ ለማክሰኞ ጥቅምት 5 ቀን 2006 ዓ.ም. ሰበር ሰሚ ችሎት እንደሚሰየም ጋዜጣው ቢዘግብም የማክሰኞ ችሎት ውሎውን በመለከተ ግን ያለው ነገር የለም፡፡ እንደጋዜጣው ዘገባ ከሆነ ፤ ዑለማዎች ምክር ቤት በራሱ በእስልምና ጠቅላይ ጉባዔዎች ስር ያለ በመሆኑ እና የነዚህ የበላይ ደግሞ መጅሊሱ በመሆኑ ዑለማዎች ምክር ቤት የማስመረጥ መብት የለውም የሚለው የክሱ አንዱ ጭብጥ መሆኑን ጠበቃ ተማም መናገራቸው ተዘግቧል፡፡
እንደጠበቃ ተማም ገለፃ፤ ዑለማዎች ምክር ቤት ምርጫ ያካሄደው የራሱ የሆነ ህጋዊ ሰውነት ሳይኖረው ነው፡፡ ምርጫውን የማካሄድ ስልጣን የዑለማዎች ምክር ቤት ሊሆን አይችልም፡፡ ምርጫው አስመራጭ በሌለበት ሁኔታ ሊደረግ አይችልም፡፡ ለዚህም አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣውን ሁሉ በማስረጃነት አቅርበናል በማለት የክሳቸውን ዝርዝር ጠቁመዋል፡፡
ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከቀረቡ የክስ ፋይሎች መካከል ፤ ጅሃዳዊ ሃረካትን በተመለከተ በኢቴቪ የቀረበው ዘጋቢ ፊልም፣ ፌደራል ፖሊስ፣ ደህንነት፣ ከፍተኛ ፍርድ ቤትን እና የከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት ተከሰው የነበረ ቢሆንም፤
ፍርድ ቤቱ የዘጋቸው ፋይሎች በሰበር ችሎቱ በድጋሚ እንደሚቀርቡ ይጠበቃል ሲል ጋዜጣው ዘግቧል፡፡