ሰሜን ሸዋ አማራውና ኦሮሞው በአንድነት ቆሞ ወያኔን እየተፋለመ ነው

October 20, 2017

ሙሉቀን ተስፋው

አገዛዙ በዴራ ሰሜን ሸዋ ዐማራና ኦሮሞን ለማጋጨት የሸረበው ሴራ ከሸፈ፤ የ3 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

በሰሜን ሸዋ ዴራ ትናንት የዐማራና የኦሮሞ ተወላጆችን ለማጋጨት በአገዛዙ የተሸረበው ሴራ ሙሉ በሙሉ የከሸፈ ሲሆን በአገዛዙ ኃይሎች የሦስት ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡ ትናንት ጥቅምት 9 ቀን 2010 ዓ.ም ከጠዋት ጀምሮ በዴራና በመራህቤቴ የተለያዩ አካባቢዎች ከፍተኛ ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ተካሒደዋል፡፡

በተቃውሞው 7 ሰዎች በጥይት ተመትተው የሁለቱ ሕይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ አንደኛው መራቤቴ ሆስፒታል ቢደርስም መትረፍ ባለመቻሉ የሟቾች ቁጥር ሦስት ደርሷል፡፡ ቀሪዎቹ 4ቱ ደግሞ በሪፈራል ወደ ደብረ ብርሃን ሆስፒታል ተልከዋል፡፡
የአገዛዙ ኃይሎች ከቱቲ የመጡ ዐማሮች ኦሮሞዎችን ሊያጠፉ ነው ብለው ቢሰብኩም ‹‹ሁላችንም አንድ ነን›› በሚል ከመራህቤቴ፣ ብቸናና ዴራ የተሰባሰቡ ዐማሮችና ኦሮሞዎች ዛሬም ከአገዛዙ ኃይሎች ጋር ሲጋፈጡ መዋላቸውን ከቦታው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የመራህቤቴ ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአጋዚ ወታደር እንደተከከበ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

Previous Story

ጥያቄ:- ወያኔ የተባለዉ አረም ከኢትዮጵያ ሳይነቀል የጣና አረም ተነቅሎ ጣና ሊድን ይችላል? የአማራ እና የኦሮሞ ወጣት የትብብር ማዕከል ምን መሆን አለበት?

Next Story

በአዲስ አበባ በአንድ ዓመት ውስጥ ከ800 በላይ ቤቶች በመንግስት ፈርሰዋል

Go toTop