በትግራይ እንደርታ ሙስናን ያጋለጠ የሕወሓት አባል ተባረረ

October 5, 2013

አብርሃ ደስታ ከመቀሌ እንደዘገበው፦
በትግራይ እንደርታ ወረዳ ነው። የህወሓት አባላት የሆኑ የወረዳው አስተዳዳሪዎች (የዞኑ ሓላፊ ባለበት) እርስበርሳቸው እየተገማገሙ ሳለ አንድ አባል የወረዳው አስተዳዳሪ የ10 ሺ ብር ሙስና ከህዝብ መቀበሉ ያጋልጣል።
የህወሓት ባለስልጣናትም እርስበርስ ተነጋግረውና ተባብረው የ10 ሺ ብር ሙስና ያጋለጠ አባል እንዲባረር ወሰኑ። ተባረረ። አዎ! አብዛኛው አባል በሙስና ከተጨማለቀ የቅጣት ሰለባ የሚሆን ሙስና ያልሰራ ሰው ነው።
ህወሓቶች ሙስና ያጋለጠ አባል ከአባልነት በማባረር ድርጅቱ የሙስና ካምፕ ለማድረግ ያሰቡ ይመስላል። መቼም ሙስና የሚያጋልጡ ሰዎች በማራቅ ሙስናን ማንገስ እንጂ መታገል የሚቻል አይመስለኝም።
ለነገሩ ህወሓቶች ሙስናን ላለመጋለጥ ተስማምተው የለ። ሙሰኛ መቅጣት ከተጀመረ ማን ማንን ሊቀጣ? አስቸጋሪ ነው። ሙሰኛ ለሙሰኛ እንዴት መቅጣት ይቻለዋል? እንደውም ሙሰኞች ተሰባስበው ሙሰኛ ላልሆነ አባል መቅጣት ይቀላቸዋል። እንዲህም እያደረጉ ነው።
ሙሰኛ ስርዓት ሙስናን መቃወም አይችልም። ምክንያቱም ሙስና ለማጥፋት ሙሰኞች ማጥፋት ግድ ይላል። ለገዢዎች ራስ ማጥፋት ከባድ ነው።

የሕዝብ አስተያየት፦

ታዲያ በዚህ ዓይነት እንዴት አዜብ መስፍንን ማጋለጥ ይቻላል?


Previous Story

መሬት የማነው? – ከፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

Next Story

የማለዳ ወግ … በጋዜጠኛና ደራሲ ተስፋየ ገብረ አብ ላይ የቀረበው ክስ መረጃ አንድ እውነታ – ከነቢዩ ሲራክ

Go toTop