(ትንሣኤ ራድዮ) የሱዳንና የወያኔ የመከላከያ መኮንኖች በሁለቱ አገሮች ድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚዎችን ለመቆጣጠር ስለሚቻልበት ሁኔታ ለመምከር አሶሳ ውስጥ ስብሰባ አደረጉ:: የሁለቱ አገራት መኮንኖች በሳምንቱ መግቢያ ላይ በቤንሻንጉል ጉሙዝ አሶሳ ከተማ ላይ ባደረጉት የሁለት ቀናት ስብሰባ፣ በሱዳን እና በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የነጻነት ሃይሎችን ስለሚቆጣጠሩበት ሁኔታ መክረዋል።
በምእራብ እዝ አዛዡ በተመራው ስብሰባ ወያኔ ለሱዳን መንግስት ተማጽኖ አቅርቧል። ከሱዳን እየተነሱ ጥቃት የሚፈጽሙ፣ የሁለቱም አገራት ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያውያን እየተለዩ ቁጥጥር እንዲደረግባቸው በወያኔ በኩል ሃሳብ ቢቀርብም፣ በሱዳን በኩል ሱዳናዊ ዜግነት ያላቸውን የኢትዮጵያውያን ዜግነት ካላቸው ጋር ለመየት አስቸጋሪ መሆኑን በመግልጽ፣ የመለየቱ ስራ በጥንቃቄ እንዲካሄድ መክረዋል።
የሱዳን መኮንኖች ከወያኔ መኮንኖች ጋር ስብሰባ ማድረጋቸው እንዳይታወቅባቸው፣ የወያኔ መኮንኖች የለበሱትን ወታደራዊ ዩኒፎርም እንዲለብሱ ተደርጓል።