አንድነት ፓርቲ በመስከረም 05 ሊያካሂድ የነበረው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ፣ በመንግስት ዕውቅና አግኝቶ ለመስከረም 19 ተላለፈ!

September 13, 2013

አንድነት ፓርቲ በመስከረም 05 ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱ ይታወቃል፡፡ ይሁን አንጂ መንግስት ሁለት ምክንያቶች በማቅረብ ለሐምሌ 19 እንዲተላለፍ ጠይቋል፡፡ በመስቀል አደባባይ አካባቢ በባቡር ግንባታ ምክንያት የታጠሩ ቆርቆሮዎችን ለማንሳትና አዲሱን ዓመት አስመልክቶ በአካባቢው ባዛር እየተደረገ በመሆኑ መንግስት እንዲራዘም ጠይቋል፡፡ ለመንግስት በአዋጅ የተሰጠው ስልጣን በቂ ምክንያት ሲቀርብ እንዲያራዝም ህጉ የሚፈቅድ በመሆኑ ፓርቲያችን ህግን ተከትሎ ተቀብሎታል፡፡

ስለሆነም ይህ ከመንግስት እውቅና የተሰጠውን ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ መስከረም 19 በደማቅ ሁኔታ ይካሄዳል፡፡ ሰልፉ ከ23 የአንድነት የአዲስ አበባ መዋቅር አደረጃጀቶች ተነስቶ ወደ መስቀል አደባባይ ይተማል፡፡ በዚህ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ የአዲስ አበባ ነዋሪ በነቂስ ወጥቶ ብሶቱን እዲገልፅ አንድነት ፓርቲ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ድል የሕዝብ ነው!

Previous Story

የፖለቲካ ካሊፕሶ – “ከፕ/ት ግርማ ይልቅ ቴዲ አፍሮ አስመራ ቢሄድ ይሻል ነበር” – (ከተስፋዬ ገብረአብ)

Next Story

ራዕይ ነበረው፣ ተቀጥሎበታልም።

Go toTop