(ዘ-ሐበሻ) በ2014 ኦክቶበር ወር ላይ ‹‹መንግስት ይገድላል፣ ያፍናል፣ ይጨቁናል” ብሎ ጽፏል; እንዲሁም በሌሎች ተጨማሪ 2 በተከሰሰባቸው 3 ክሶች የ3 ዓመት እስራት የተፈረደበት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሊፈታ መሆኑ ተሰማ::
ከቤተሰቦቹ አካባቢ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለከተው ጋዜጠኛ ተመስገን የ እስር ጊዜውን ጨርሶ በአመክሮ ከ13 ቀን በኋላ ይፈታል::
ዓ.ም የመንግስትን ስም ማጥፋት፣ ህዝብን ማነሳሳትና የህዝብን አመለካከት ማናወጽ በሚሉ ሶስት ክሶች ጥፋተኛ ተብሎ የነበረው ተመስገን በተፈረደበት ወቅት አንዳችም የቅጣት ማቅለያ እንዳላቀረበ ይታወቃል::
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በ እስር ቤት ቆይታው የተለያዩ ስቃዮች ሲደርሱበት እንደነበር ዘ-ሐበሻ በተደጋጋሚ መዘገቧ አይዘነጋም::