ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ በአየርመንገድ በኩል በርካታ የታሸጉ ነገሮች እየሄዱ ነው

August 9, 2016
Addis Ababa Airport

(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ ኤርፖርት የሚገኙ የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንዳስታወቁት ካለፈው እሁድ ጀምሮ ከአዲስ አበባ ወደ ትግራይ ምንነቱ ያልታወቀ የታሸገ ፓኬጅ በብዛት ወደ መቀሌ እየተጓጓዘ ነው::

ምኝጮቹ እንደሚሉት ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ እየተጓጓዘ ያለው ምናልባትም ውድ የሆኑ የሃገሪቱ ንብረቶች; ገንዘብ እና ወርቅ ሊሆን ይችላል:: እነዚህ የታሸጉ እቃዎች በኤርፖርት በኩል ወደ መቀሌ ሲጓዙ ከፍተኛ የሆነ ጥበቃ እንደሚደረግና የሌላ ብሄር ተወላጆች እንዳያዩ እንደሚገሸሹ እነዚሁ ምንጮች አስታውቀዋል:: ፓኬጆቹን ጭነው የሚሄዱት አብራሪዎችም የትግራይ ክልል ተወላጅ የሆኑ ብቻ ናቸው ተብሏል::

በተለይ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች የተፈጠረው የሕዝብ ማዕበል ሳይበላን እቃችንን እናሽሽ ይመስላል የሚሉት እነዚሁ ምንጮች በጣም ውድ የሆኑ ነገሮች ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ በብዛት እየተሸጋገረ መሆኑ በአየር መንገዱ ውስጥ መናገገሪያ ሆኗል ብለዋል::

Previous Story

ወገኖቻችንን ለዘመናተ የጨረሰው አደገኛው ዘንዶ፡-የኢትዮጵያ ሕገ-መንግስት – ሰርጸ ደስታ

Next Story

ወልቃይት የማን ነው? የማይረባ ጥያቄ | ከፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

Go toTop