ጥሩነሽ ዲባባ – ጠይሟ ልዕልት

ጠይሟ ልዕልት
የሩጫው ድማሚት
ሰዓት ጠብቃ ስትፈነዳ
አንድም ታምራለች እንደ ጽጌሬዳ
አንድም ታርዳለች እንደ ካባው ናዳ ፡፡
ጠይሟ ቀስተ ዳመና
ባለብዙ ልዕልና
የስንቱን አይን በረገደች ?
በወቸው ጉድ በለጠጠች ::
የስንቱን ልብ አሞቀች ?
በፍቅር መዳፍ ጣለች ::
እናትስ ትውለድ ያንቺን አይነቱን አቦሸማኔ
ህዝብ የሚወድ አስተኔ ፡፡

ከአለማየሁ ገበየሁ

Previous Story

ኢሳት ያኣማራ ቊጥር የቀነሰበትን ምክንያት አጋለጠ:

Next Story

ሙስሊም ወገኖቻችንን የሚያዋከወበውንና የሚያሸብረውን የወያኔ/ኢህአዴግ ተግባር እናውግዝ፣

Go toTop