Hiber Radio: ጌታቸው ረዳ በአባይ ግድብ ዙሪያ የሰጡት ያልተገራ አስተያየት የካይሮ ባልስልጣናትን አስቆጣ * ከጋምቤላ የታፈኑት ህጻናት በደ/ሱዳን ለሽያጭ ሳይቀርቡ እንዳልቀረ ተሰግቷል

May 30, 2016
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

<...አሁን ያለው አስተዳደር አንድ ቅርጽ ይዞ እንደ መንግስት የሚሰራ ሳይሆን ጥቂት ግለሰቦች እና ቡድኖች በዙሪያቸው ባሰባሰቧቸው ተጠቃሚዎች የሚመራ የጠባብና ዘረኛ ቡድን የሚያሽከረክሯት አገር ነች።...ግንቦት ሃያን የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚመለከተው እንደ ክፉ ቀን የመጣበት፣ዘረኝነት የተስፋፋበት ፣ሙስና የተስፋፋበት ነው … እነሱ ሃያ አምስት ሲያከብሩ እኛ አንድ ብለን በጋራ ለለውጥ የተምንነሳበት ወሳኝ ወቅት ነው ይህ ካልሆነ ግን...> አቶ ግርማ በቀለ የኦሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ሕብረት ሊቀመንበር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከአገር ቤት ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

<...በመኢአድ ስም የተጠራው ጉባዔ ያው የተለመደ ሕገ ወጥ ተግባር አካል ነው።ሕጋዊ የመኢአድ የም/ቤት አባላት አልተጠሩም ። ከዚህ ቀደም ከአንዴም ሁለቴ የተደረገውን ከመላው አገሪቱ የተሰባሰቡ ሕጋዊ የመኢአድ አመራሮች የተሳተፉበትን በራሱ በምርጫ ቦርድ ጥያቄ ከአንዴ ሁለቴ የተደረገውን ጉባዔ ውጤት ሰርዘው ሕጋዊውን አመራር በፖሊስ ከጽ/ቤት አባረው ከቤቱ አምጥተው የሾሙት ነው ዛሬ ስልጣኑን ለማራዘም የብአዴን አባላትን ሰብስቦ ጉባዔ ጠራሁ ያለው።ህግን መሰረት ያላደረገ ነው...በተቃዋሚዎች ላይ የሚወስዱት እርምጃ ስርዓቱ እንዳሰበው አላጠነከረውም ሕዝቡ የራሱን ትግል እየመረጠ ነው ።በቃኝ ብሏል...> አቶ ማሙሸት አማረ የሕጋዊው መኢአድ ፕሬዝዳንት ለህብር ከሰጡት ቃለ መጠይቅ (ሙሉውን ያዳምጡት)

በቬጋስ ተጠርቶ ውቴታማ ያልሆነው የሁበር አሽከርካሪዎች ተቃውሞና ተያያዥ ጉዳዮች

የዛሬ ስድስት ዓመት በኡጋንዳ ከሚገኝ የኢትዮጵያ ሬስቶራንት ላይ ጥቃት በማድረስ የሰው ሕይወት የቀጠፉ አሸባሪዎች ሰሞዩን የተላለፈባቸው ውሳኔ ሲዳሰስ(ልዩ ዘገባ)

በኢሚግሬሽን እስር ቤት ስላሉት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ በዝዋይ እስር ቤት የጻፍከው ጽሑፍ ተገኘ በሚል ጨለማ ቤት እንዲገባ ተደረገ

ከጋምቤላ የታፈኑት ጨቅላ ህጻናት በደ/ሱዳን ውስጥ ለሽያጭ ሳይቀረቡ እንዳልቀረ ተሰግቷል

የአሜሪካ ሴኔተሮችና ዲፕሎማቶች በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ዙሪያ የተሰማቸውን ስጋትጋት ገለጹ

በተለጣፊው መኢአድ ስም የተጠራው ጉባዔ የስርዓቱ ሕገ ወጥ ተግባር አካል መሆኑን ተቃባይነት እንደሌለው ሕጋዊው የፓርቲው ፕሬዝዳንት ገለጹ

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ለዓለም ጤና ድርጅት መሪነት እሾማለሁ ማለት በአገሪቱ ለሚደረገው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና በጤና ስም ሲደረግ የነበረውን ሙስና መደገፍ ነው ሲሉ ከአገር ቤት አንድ የተቃዋሚ መሪ ገለጹ

የኢህአዲጉ የኮሚኒኬሽን ሚኒስተር ጌታቸው ረዳ በሕዳሴው ግድብ ግንባታ ላይ የሰጡት ያልተገራ አስተያየት የካይሮ ባልስልጣናትን አሰቆጣ

የኢትዮጵያው አገዛዝ የኤርትራ ተቃወሚዎችን በገንዘብ ለመርዳትና ለማደራጀት መወሰኑ ታወቀ

በሜዲትራኒያን ባህር ሰሞኑን የሰጠሙት ስደተኞች ቁጥር ከሰባት መቶ በላይ ሊሆን እንደሚችል ስጋት አለ

የስፔኑ ሃያል የእግር ኳስ ቡድን ሪያል ማድሪድ ኣትሌቲኮ ማድሪድን በማሸነፈ በአውሮፓ ሻምፒዮና ውድድር ታሪክ ሰራ

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የባፍሎ ዓመታዊ የማራቶን ውድድር አሸናፊ ሆኑ

እና ሌሎችም ዜናዎች አሉን

Previous Story

ባለፈው 15 ቀናት ብቻ 2 ሴቶችና 5 ወንዶች የግንቦት 7 እና ኦነግ አባል ናችሁ ተብለው በአ.አ ኤርፖርት ታስረዋል

Next Story

ፈተናን መስረቅ ለስብሃት ነጋ ትግል ለሌላው ወንጀል ያደረገው ማነው?

Go toTop