የጅንካ ከተማ ወጣቶች ከአንድነት አባላት ጋር በመቀናጀት እየቀሰቀሱ ነው

August 1, 2013

የጅንካ ወጣቶች ታሪክ እየሰሩ ነው፡፡ አንድነት ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ በንቃት ለመሳተፍ ከመንቀሳቀሳቸውም በላይ በጅንካና በአካባቢዋ በራሳቸው ተነሳሽነት ቅስቀሳ እያከናወኑ ነው፡፡

በተያያዘ ዜና የደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሞሎካ ውብነህ በ22/11/2005 ዓ.ም በቁጥር 417/107/05 በፃፉት ደብዳቤ ለአንድነት አመራሮች የእንወያይ ጥሪ አድርገው ከ14 የሀገር ሽማግሌዎችና ከጅንካ ከተማ ከንቲባና የተለያዩ የከተማው ባለስልጣናት ጋር በመሆን አንድነት ሰላማዊ ሰልፉን መሰረዝ አለበት በማለት ለማግባባት ሞክረዋል፡፡ የአንድነት አመራሮችም “ሰላማዊ ሰልፉ አይቀርም መብታችንን አሳልፈን አንሰጣችሁም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

የጂንካ ከተማ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) አመራሮችና አባሎች ከኦሞ ሕዝቦች ፓርቲ 1 አባል እንዲሁም ከሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ 1 አንድ አባል የተካተቱበት ኮሚቴ በማዋቀር ሐምሌ 28,2005 ዓ.ም የሚደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ የማስተባበር ስራ  ከሐምሌ 15 ቀን 2005 ዓ.ም አንስቶ መጀመራቸው አይዘነጋም፡፡ #millionsofvoicesforfreedom #Ethiopia #UDJ

Previous Story

የሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በከፋፋዮች ሴራ አትናወጥም!!! ለአንድነት ከቆሙ ምእመናን

Next Story

ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በጀርመን ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ

Go toTop