ጊዜው ሩቅ ቢሆንም ዛሬም ትዝ የሚለኝ ነገር ታማኝን መጀመሪያ ያየሁበት ቀን ነው። አንድ ወዳጄ ብሄራዊ ትያትር የቅዳሜውን የጠዋት ሲኒማ ለማየት ተቃጥረናል። በ1970 መጨረሻ ላይ ብሄራዊ ትያትር በተለይ ቅዳሜ ጠዋት ጥሩ ጥሩ ፊልሞችን ያሳየን ነበር። እዚያ ነበር ታማኝን ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት። ከብሔራዊ ትያትሩ አንድ ሁለት ደጃፍ አለፍ ብሎ አንድ ካፌ ነበር። እዚያ በዘመኑ አለን የምላቸው አርቲስቶች ሻይ ቡና የማለት ልምድ አላቸው። ከወዳጄ ጋር ቁጭ ብለን የሲኒማ ቤቱን መከፈት በሻይ ቡና አጅበን ስንጠብቅ ድንገት ነበር ሄ ቀጭን ልጅ ብቅ ያለው። ሲያዩት የከተማ አራዳ የሚመስለው ልጅ ድንገት በቁሙ አንድ ስኒ ቡና ጠትቶ ከመውጣቱ በፊት አብሮን የነበረው ወዳጄ ታውቀዋለህ? ያለኝ። ጓደኛዬ የኔን አሉታ መልስ ከሰማ በኋላ አያይዞ ማብራሪያ ሰጠኝ። (ሙሉውን ለማንበብ እባክዎ እዚህ ይጫኑ)