ወደ ሃዋሳ ለድጋፍ ሲሄዱ በመኪና አደጋ የሞቱት ወጣቶች ፎቶ ግራፍ ይመልከቱ

July 8, 2013

ዘ-ሐበሻ በትናንት ዘገባዋ ወደ አዋሳ ሲጓዙ በነበረ የቅ/ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ላይ በደረሰ የመኪና አደጋ የሰዎች ሕይወት ጠፋ ስትል መዘገቧ አይዘነጋም። ዛሬ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ባገኘነው መረጃ መሠረት የሁለቱ ሟች ወጣቶች ፎቶ ግራፍ እና ስም ደርሶናል።
አንደኛው ሟች መሃሪ የሚሰኝ ሲሆን የዚህ ወጣት የፍትሃትና የመታሰቢያ መርሃ ግብር የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋቾች በተገኙበት ጉርድ ሾላ በሚግኘው በሰሃሊተ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል። የቀብር ስነስር ዓቱም በነገው እለት ይፈጸማል ተብሎ ይጠበቃል።
ሌላኛው ደጋፊ ደግሞ ሲሳይ ይሰኛል። የዚህም ወጣት ቀብር ስነስርዓት የት እና መቼ እንደሚፈጸም እያጣራን ነው።

ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን፤ ለተጎዱት ፈጣን ምህረትን ለሟቾች ገነትን ጌታ እንዲሰጣቸው ዘ-ሐበሻ ትመኛለች።

Previous Story

ሸንጎ 2ኛውን መደበኛ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቁን ገለጸ

Next Story

Hiber Radio: የደሴውን የአህባሽ ደጋፊ ሼህ ስርዓቱ ለፖለቲካ ትርፍ ሲል እንደገደላቸው የዕምነቱ ተከታዮች እየገለጹ ነው

Go toTop