አበበ ገላው ተጫማሪ የግድያ ዛቻ ደረሰው

February 17, 2013

(ዘ-ሐበሻ) ጋዜጠኛ አበበ ገላው ተጨማሪ የግድያ ሙከራ ዛቻ እንደደረሰው በጎግል ቮይስ በኩል በድምጽ ማስረጃ አቀረበ። “አበበ ደምህን እንጠጣዋለን፤ ከኛ የትም አታመልጥም” ሲል አስፈራሪው ሰው ይሰማል። ይህን ተከትሎ አበበ በፌስቡክ ገጹ እንዳለው “የህወሃቶች ዛቻ እና የዘረኝነት ፉከራ ቀጥሏል። እስከ አሁን ያልተገለጠላቸው ሃቅ እንኳን ዛቻ ሞት ከትግላችንም ሆነ ከቁርጠኛ ጉዞአችን ፈጽሞ አይገታንም። ነጻነት ወይንም ሞት ብሎ የተነሳን ህዝብ ማንም አንባገነን አያስቆመውም። እኔ ብሞትም በዛ በታላቅ አደባባይ ላይ የተናገርኩት እውነት ግን ፈጽሞ አይሞትም፣ ምክንያቱም በያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ የታመቀ ሃቅ ነውና። ሃቅ ሲታፈን ፈንድቶ መውጣቱ ያለ እና ወደፊትም የሚኖር ነው።”

የድምጽ ማስፈራሪያውን ለማድመጥ እዚህ ይጫኑ
አስተያየታችሁን እንጠብቃለን።

Previous Story

ደራሲው ያልተገለጸው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አሳፋሪ ፊልም “ጀሀዳዊ ሃራካት”

Next Story

አዜብ መስፍን የአዲስ አበባ ከንቲባ?

Go toTop