Hiber Radio: የሰማያዊ ፓርቲው ዮናታን ተስፋዬ “መተማመኛችን ሕዝብ ነው” ማለታቸው… ወ/ሮ ፀዳለ እጅጉ እና ወ/ሮ ወሰንየለሽ ደበላ የአለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ ቃለምልልስ መስጠታቸው… እነአብርሃ ደስታ ችሎት ደፍራችኋል ተብለው ሊፈረድባቸው መሆኑ… ኦባማ የዛሬ ሃምሳ ዓመት ለነፃነት የተጀመረው መስዋዕትነት ዛሬም አልተጠናቀቀም ማለታቸው… ድምፃችን ይሰማ በእስር ካሉት የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት አገዛዙ ከህዝብ መነጠል እንደማይችል መግለጹና ሌሎችም –

March 10, 2015
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ የካቲት 29 ቀን 2007 ፕሮግራም
እንኳን ለአለም አቀፍ የሴቶች ቀን አደረሳችሁ
<…የአውሮፓ ህብረት አገራት አምባሳደሮች በየጊዜው ለሚያቀርቡልን ጥያቄ በርግጥ የኢትዮጵያ ጉዳይ ይህን ያህል የሚያሳስባችሁ ከሆነ ከከንፈር መጠጣ ያለፈ ጠንካራ እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቀናል …. ዋናው መተማመኛችን ህዝብ ነው…> አቶ ዮናታን ተስፋየ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የፓርቲው ፕሬዝዳንት የአውሮፓ ህብረት አገራት በኢትዮጵያው አገዛዝ ላይ ጠንካራ እርምጃ እንዲወስዱ መጠየቃቸውን በተመለከተና ተያያዥ ጉዳዮች ከህብር ሬዲዮ ተጠይቀው ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡ )
<…የኢትዮጵያ ሴቶች ጥያቄ የዲሞክራሲ ጥያቄ በመሆኑ በአገሪቷ ላይ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እስካልመጣ ድረስ የሴቶችም የሃይማኖትም የብሄርም ጥያቄ ምላሽ አያገኝም… ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙን ጨምሮ ስርዓቱ የመብት ጥያቄ ባነሱ ሴቶች ላይ የሚፈፅመው ግፍ ሊያቆም የሚችለው…..> ወ/ሮ ፀዳለ እጅጉ እና ወ/ሮ ወሰንየለሽ ደበላ የአለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ ከነበረን ቆይታ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡ )
የአለማችን ድሃው ፕሬዝዳንት ከስልጣን መልቀቅ (ልዩ ዘገባ)
የፍራይዝ አሽከርካሪዎችን የፍርድ ሂደትን በተመለከተ (ቃለ መጠይቅ) ሌሎችም
ዜናዎቻችን
በኢትዮጵያ በሽብር ተጠርጥሮ በእስር ላይ የሚገኝ የእንግሊዝ ዜግነት ያለው ግለሰብ ከአይሲስ ቀንደኛ አባል ጋር ግንኙነት ነበረው ሲል የአገሬው ጋዜጣ ዘገበ
ከአገዛዙ ፍርድ ቤት ፍትህ ስለማልጠብቅ ጠበቃዬን አሰናብቻለሁ ያለውን አብርሃ ደስታን ጨምሮ የሺዋስ አሰፋና ዳንኤል ሺበሺ ችሎት ደፍራችኋል በሚል በነገው ዕለት ሊፈርድባቸው ቀጠሮ ተይዟል
የእንግሊዝ ግብር ከፋዮች ገንዘብ ኢትዮጵያ ውስጥ ለአፈና እየዋለ ነው በሚል በአገሪቱ ላይ ክስ የመሰረተው ኢትዮጵያዊ አርሶ አደር ክሴን አንስቻለሁ አለ
የክሱ መነሾ ጥያቄው ምላሽ ስላገኘ መሆኑን ገልጿል
ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ የዛሬ ሃምሳ ዓመት ለነፃነት የተጀመረው መስዋዕትነት ዛሬም አልተጠናቀቀም ዜጎች ለሰላማዊ ለውጥ ሊታገሉ ይገባል ሲሉ ጥሪ አቀረቡ
የአገዛዙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በውሸት ለሰሩት ፕሮፓጋንዳ ህፃንዋን ተጠያቂ ለማድረግ መሞከራቸው አሳፋሪ መሆኑን ኢትዮጵያውያን በመግለፅ ላይ ናቸው
ድምፃችን ይሰማ በእስር ካሉት የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት አገዛዙ ከህዝብ መነጠል እንደማይችል ገለፀ

Previous Story

ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹ኢህአዴግ›› በሚል ስም የተመዘገቡ ሁሉም ዕጩዎች እንዲሰረዙ ጠየቀ

Next Story

ወያኔና ሽብርተኛነት – መስፍን ወልደ ማርያም

Go toTop