‹‹ኢህአዴግና ምርጫ ቦርድ አንድነትንና ሰማያዊን አዋህደዋቸዋል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

February 3, 2015

የአንድነት መዋቅር በጣም ብዙ ነው፡፡ በየ ክፍለሀገሩ (በጎንደር፣ በወሎ፣ በጎጃም፣ በደቡብ ኢትዮጵያና በሌሎቹም) ለምዝገባ በተንቀሳቀስንበት ወቅት አብዛኛዎቹ በብዙ መንገድ ተባባረውናል፣ በግልጽም ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር እየሰሩ ነው፡፡ ብዙዎቹም እኛ በሌለን ቦታ ላይ የሰማያዊ ፓርቲን ፎርም ሞልተው ቀድመው ተመዝግበዋል፡፡ ይህን ስል ደግሞ ሰማያዊ በህግ ይህን የማድረግም መብት ስላለን ነው፡፡ የሰማያዊ ስራ አስፈጻሚ አንድ አባል ሙሉ አባል ለመሆን 6 ሳምንት መጠበቅ አለበት የሚለው አስፈላጊ ነው ብሎ ሲያምን ይህን በአንድ ቀን ውስጥ አባል የማድረግ ስልጣን አለው፡፡ በዚህ ደንባዊ አካሄድ የአንድነት አባላት በኢህአዴግና በምርጫ ቦርድ በፓርቲያቸው ላይ ባደረሰባቸው ችግር በአንድ ቀን አባል እንዲሆኑ ወስነናል፡፡

ስለዚህ ጉዳይ ከእነ በላይና ተክሌም ጋር ረዘም ላለ ጊዜ ውይይት አድርገንበታል፡፡ የአንድነት አባላት በግል መጡ የሚባለው ለህግ ሲባል እንጅ ብዙዎቹ የአንድነት አባላት እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ከዛሬ ቀደም ብለው ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር አብረው እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
ነገር ለበጎ ነው ይባላል፡፡ እነዚህ ሁለት ፓርቲዎች እንዴት እርስ በእርሳቸው ይወዳደራሉ? ተመሳሳይና ተቀራራቢ ፕሮግራም እያላቸው ለምን አንድ አይሆኑም? እየተባለ ከህዝቡም ከጋዜጠኞችም ጥያቄ ሲመጣ ቆይቷል፡፡ በአንድ በኩል ኢህአዴግና ምርጫ ቦርድ ተቃዋሚዎችን አዳከምን ብለው በአንድነት ላይ ውሳኔ ሲያስተላልፉ ሁለቱን አንድነትና ሰማያዊን አዋህደዋቸዋል ማለት እችላለሁ፡፡ ከዚህም በኋላ ሰማያዊ እነሱን የሚያሳትፍ አመራር በመፍጠር በምክር ቤትም፣ በስራ አስፈጻሚም ሆነ በሌሎች ቦታዎች ችሎታቸውና ብቃታቸው መሰረት በማድረግ እንዲሰሩ የሰማያዊ አመራር ክፍት መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፡፡ የአንድነት አባላት በብቃታቸው በየቦታው ተመድበው እንዲሰሩ አስፈላጊውን ሁሉና ቀናነት ያለው አመራር እንደምናደርግ ይህን ትግል ለተቀላቀላችሁ አባላት ቃል እገባለሁ፡፡
ምንጭ :- ነገረ-ኢትዮጵያ

Previous Story

Hiber Radio: በደቡብ አፍሪካ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደረገው ዘረፋ መቀጠሉና 3 ወገኖቻችን መቁሰላቸው… በኢትዮጵያ ለውጥ ለማምጣት የፓርቲ ፖለቲካ ሳይሆን ሕዝባዊ ትግል እንደሚያስፈልግ መገለጹ… ገዢው ፓርቲ አንዳርጋቸው ጽጌን ለፖለቲካ መጠቀሚያነት ማዋሉን የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች መቃወማቸው.. ኢትዮጵያ ዛሬም በአቶ መለስ የሙት መንፈስ እንደምትመራ የአገዛዙ ሚዲያ ዘገባ ማመልከቱ ና ሌሎችም

Next Story

ሴቶች በባሎቻቸው ላይ የሚሄዱባቸው 7 ምክንያቶች [Top 7 Reasons Why Women Cheat]

Go toTop