በአፋር ክልል የመከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊሶች ከሶማሌው ዒሳ ጎሳ ጋር ተዋግተው 3 ሰዎች መሞታቸው ተዘገበ

October 4, 2014

አኩ ኢብን አፋር ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው፦

በአፋር ክልል በኡንዳ ፎኦ ከተማ የመከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊሶች ከሶማሌው ዒሳ ጎሳ ጋር የተዋጉ ሲሆን በግጭቱም 3 ሰዎች ሲሞቱ ከ20 በላይ መቁሰላቸው ታውቋል። ከሁለት ቀናት በፊት በደቡብ አፋር ኡንዳ ፎኦ ከተማ የሚኖሩ የሶማሌ ተወላጅ የኢሳ ጎሳዎች በመጀመሪያ ከፈደራል ፖሊሶች ጋር የተዋጉ ሲሆን ከፖሊስ አንድ ሰው ሲሞት ወደ 18 የሚጠጉ ቆስለዋል።

በኋላ ላይ የአገር መከላከያ ሰራዊት ሃይል የደረሰ ሲሆን ከኢሳዎች ሁለት ሰዎች ገድሏል። ሁለት የመከላከያ አባላት ደግሞ በከፉኛ ቆስለዋል። የውግያው መነሻ የሆነው በቅርብ ጊዜ በፈደራል ጉዳዮች የተወሰነው የመሬት ጉዳይ ሲሆን መሬቱን ለአፋር ክልል መንግስትና ህዝብ ለማስረከብ የተወሰነው ውሳኔ መሆኑን ምንጮቻችን ዘግበዋል።

Previous Story

የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች 28 ቀን ተቀጠረባቸው • በሽብርተኝነት ተጠርጥረው የተያዙ ሌሎች 10 ያህል ዜጎችም ቀርበዋል

Next Story

የወያኔው ወመኔዎች መንግስት የደህንነት ቡድን በድጋሚ በአዲስ መልክ ተዋቀረ

Go toTop