“ዶ/ር ኢንጂነር” ሳሙኤል ዘሚካኤል ኬኒያ ላይ ተይዞ ወደ ሃገር ሊመለስ ነው ተባለ

July 29, 2014

(ዘ-ሐበሻ) አነጋጋሪው ‘ዶ/ር ኢንጂነር ሳሙኤል ዘሚካኤል’ ኬንያ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሉን እና ወደሃገር ቤትም እንደሚመለስ ኢቶሚካሊንክ የተባለው የራድዮ ፕሮግራም ከአዲስ አበባ አስታወቀ።

በከተማው ውስጥ የማይገባውን የትምህርት ደረጃና ማዕረግ ጭኖ ሕዝብን ሲያታልል ነበር የተባለው ሳሙኤል ዘሚካኤል በመገናኛ ብዙሃን ድርጊቱ ከተጋለጠ በኋላ በርካታ ነጋዴዎች እና ግለሰቦች በዚህ ሰው ተጭበርብረናል በሚል ክስ መመስረታቸው የታወቀ ሲሆን በኢንተርፖል አማካኝነት ከኬንያ ወደ ኢትዮጵያ ተላልፎ እንደሚመጣ ይጠበቃል።

ራድዮው እንደዘገበው ዶ/ር ኢንጂነር ሳሙኤል ዘሚካኤል ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።

Previous Story

Hiber Radio: በአንዳርጋቸውላይ የተቀናበረው ፊልም በሳቸውና በሌሎች ላይ የሚፈጸመውን ሰቆቃ አጋለጠ፤ * ድምጻችን ይሰማ የኢዱን ተቃውሞ ሰረዘ

Next Story

እረ በመድሃኔ ኣለም ይብቃዎት ኢንጂነር ግዛቸው! 

Go toTop