Hiber Radio: በአንዳርጋቸውላይ የተቀናበረው ፊልም በሳቸውና በሌሎች ላይ የሚፈጸመውን ሰቆቃ አጋለጠ፤ * ድምጻችን ይሰማ የኢዱን ተቃውሞ ሰረዘ

July 28, 2014

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
የህብር ሬዲዮ ሐምሌ20 ቀን 2006 ፕሮግራም

ለእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢድ አልጥር በዓል አደረሳችሁ

<< በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የቀረበው የአገዛዙ ፊልም ያው እንደተለመደው ተቆርጦ የተቀጠለ አቶ አንዳርጋቸው ከነበሩበት ክፍል ቀጥሎ ቶርች የሚያደርጉት ሰው የጣር ድምጽ የሚሰማበት እንዳሰቡት ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ጠቀሜታ የሌለው የስርዓቱን ማንነት የበለጠ የሚያጋልጥ ፊልም ነው...>>

ጋዜጠኛ አበበ ገላው በአቶ አንዳርጋቸው ላይ አገዛዙ ያሰራጨው አዲሱ ፊልም አስመልክቶ ከሰጠው

<.. ኢህአፓ ተመልሶ መጠናከር አለበት ኢህአፓ ዛሬም አንድ ነው ። የሽምግልና ስራ ሳይሆን የኢህአፓ ችግር ተፈቶ የተጠናከረ ድርጅት እንዲሆን ነው ።..ዓላማችንን የተረዱ ከዚህ ከአሜሪካም ከአውሮፓም አባላት እየተቀላቀሉን አንዳንዶች እየጠዩ እየመለስንላቸው ነው...> ወ/ሮ ጸዳለ እጅጉ ኢህአፓን ከ15 ዓመታቸው ጀምሮ የተቀላቀሉና በትግሉም ሜዳ ከኢህአፓ ሰራዊት አባላት አንዷ የነበሩ <<ትንሳዔ ኢህአፓ>> ብለው ከሚንቀሳቀሱት አስተባባሪዎች አንዷ ስለ እንቅስቃሴያቸው ካቀረብንላቸው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ

በዞን ላይ ላይ የቀረበው የአገዛዙ የሽብር ክስና የዓለም አቀፍ ሰባዊ ቡድኖች ተቃውሞና የ ማሪያኑ የፍርድ ቤት ውሎ(ልዩ ዘገባ)

የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ማህበር ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህንን እና የዞን ዘጠኝ ጦማሪአንን ሸለመ (የበዓሉን ጥንቅር ይዘናል)

ሌሎችም አሉ

ዜናዎቻችን

* በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የተቀናበረው አዲሱ ፊልም በሳቸውና በሌሎች ላይ የሚፈጸመውን ሰቆቃ አጋለጠ

– በፊልሙ ላይ ከአቶ አንዳርጋቸው ጀርባ ሱስት ጊዜ የሰቆቃ ድምጽ ይሰማል

– ፊልሙ ተቆርጡ ለመቀጠሉ በግልጽ ያስታውቃል

በባሌ በሲዳማ ተወላጆች ላይ ለደረሰው ችግር ኦነግና የሲዳማ ነጻነት ግንባር የህወሃት አገዛዝን የከፋፍለህ ሴራ መሆኑን በጋራ መግለጫ ገለጹ

* አቶ በረከት ስምዖን ሳውዲ አረቢአ ሆስፒታል ገቡ

– ከምርጫ 97 በሁዋላ በአእምሮ ህመም ደቡብ አፍሪካ መታከማቸው መዘገቡ ይታወሳል

ድምጻችን ይሰማ የኢዱን ተቃውሞ የአገዛዙን የሽብር ድርጊት ለማክሸፍ በሚል መሰረዙን አስታወቀ

ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ ሳውዲ ውስጥ ራሱዋን ማጥፋቷን የአገሬው ጋዜጣ ዘገበ

ኢትዮጵያ የብርን የመግዛት አቅም እንድትቀንስ ተጠየቀ

የዋጋ ግሽበቱ የሰራዊቱን አቅም እተፈታተነ መሆኑ ተገለጸ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Previous Story

የክብር ዶክትሬት ድግሪ መጠሪያ ይሆናል?

Next Story

“ዶ/ር ኢንጂነር” ሳሙኤል ዘሚካኤል ኬኒያ ላይ ተይዞ ወደ ሃገር ሊመለስ ነው ተባለ

Go toTop