ውጥረት በሰሜን ሸዋ መርሃቤቴ በርትቷል

July 21, 2014

በሰሜን ሸዋ የመርሃቤቴ ወረዳ ህዝብ ከወያኔ የፀጥታ ሃይሎችና ፌደራል ጋር ከባድ ውጊያ እያካሄደ ነው፣

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

ለወረዳው አለም ከተማና አካባቢዋ አገልግሎት ይውላል ተብሎ ከብዙ ጊዜ በሁአላ የገባውን መብራት የወያኔ መንግስት ህዝቡ የሚገለገልበትን መብራት አቁሞ ትራንስፎርሜሽኖቹን ነቅሎ ለአስቸኩአይ ጉዳይ ይፈለጋል ብሎ ወደ ትግራይ ለመውሰድ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የወረዳው 27ቱም ቀበሌ ተጠራርቶ ትራንፈርመሩን በቁጥጥር ስር በማድረግ ከላይ ከተጠቀሱት የወያኔ የፀጥታ ሃይሎች ጋር ኣሁን ድረስ ውጊኣ እያደረገ ሲሆን እስካሁን 7 የወያኔ ወታደሮች የሞቱ ሲሆን ከህዝብ ታጣቂ በኩል 1 ሞቷል።

ባሁኑ ሰዓት ወረዳውን መሉ በሙሉ የህዝቡ ታጣቂ ተቆጣጥሮት ይገኛል። ወያኔ ከአዲስ አበባና ከተለያዩ አካባቢወች ተጨማሪ ሃይል ወደ አካባቢው እያንቀሳቀሰ መሆኑ ታውቁኣል።ሁኔታው የሚመለከታችሁ ወገኖች ሁሉ እየሆነ ያለውን ሁሉ በመከታተልና አስፈላጊውን ድጋፍ እንድታደርጉ ያስፈልጋል።

Previous Story

Hiber Radio: ከአንዳርጋቸው ጽጌ መታፈን በኋላ በጎንደር እና አካባቢው የአገዛዙ ሰራዊት ቁጥር እየጨመረ መሄዱ ተገለጸ

Next Story

“በ2007 ቅማንት ራሱን ያስተዳድራል ብለን እናምናለን”

Go toTop