ሕወሓት ሪከርድ በመስበር ቄሱን በሽብር ወንጀል ከሰሰች

July 7, 2014

አብርሃ ደስታ ከመቀሌ እንደዘገበው፦

ቀሲስ ብርሃነ ቆባዕ (ከእግሪሓሪባ) በሽብር ተጠርጥረው (ከነ አደይ አልጋነሽ ጋ) ዛሬ ሰኞ ሰኔ 30, 2006 ዓም በፖሊስ ታሰሩ። ቀሲስ ብርሃነ እያረሱ እያሉ ነው በአራት ፖሊሶችና ስድስት ምልሻዎች ተከበው ከእርሻ ማሳ ታስረው ፖሊስ ጣብያ የገቡ። የነ ቀሺ ብርሃነ ጉዳይ ሽብር የሚል ነው። ህወሓት የኦርቶዶክስ ሀይማኖት አባት በሽብር በመክሰስ ሪከርድ ሰብራለች። ወይስ ቀስን በሽብር የከሰሰች ሌላ ሀገር አለች?
ጉድ ብዪ ሀገሬ ቄሱም፣ ሐጂውም፣ ኡስታዙም አሸባሪ ነው። እናቶችና የሀይማኖት አባቶች አሸባሪ ተሰኝተው የሚታሰሩበት ዘመን ደርሰናል። ካሁን በኋላ የእስልምና ሀይማኖት መሪዎች ብቻ አይደሉም በሽብርተኝነት የሚከሰሱ፤ የክርስትና ሀይማኖት አባቶችም አሸባሪዎች እየተባሉ ነው። በህወሓት ዘመን እስላም ክርስትያኑ አሸባሪ ተሰይሟል። አሁን ታድያ በሙስሊሞችና ክርስትያኖች መካከል መተባበር የሚያስፈልግ አይመስላችሁም? በቃ ሁላችን ሀይማኖት፣ ብሄር፣ ጎሳ ምናምን ሳንለይ አምባገነኑ የህወሓት ስርዓት ለመቀየር መተባበር አለብን። ሁላችን የስርዓቱ ሰለባ ነንና።
በሽብር የተከሰሱ የዓረና አባላት ቁጥር 8 ሲደርስ በተለያዩ ቦታዎች የታሰሩ የዓረና አባላት ቁጥር ደግሞ 115 ሆኗል። ቁጥሩ ለሳምንታት ታስረው የሚለቀቁና ደብዛቸው የጠፉ አይጨምርም።
ወይ ሽብር! በቃ ሁላችን አሸባሪዎች ነን።

Previous Story

“ሁለቱ ታላላቅ ዕቅዶች” ክፍል 4 (የመጨረሻ) (ዮፍታሔ)

Next Story

Hiber Radio: አ.አ አዲስ የሚገኘው የእንግሊዝ ኤምባሲ አቶ አንዳርጋቸውን የአገዛዙ ሰዎች የት እንዳደረሱ ማረጋገጫ እየጠየቅሁ ነው አለ (ልዩ ዘገባዎች በአንዳርጋቸው ዙሪያ)

Go toTop