የመቐለ ሰልፍ፥ አስፈርሙን’ኮ! (አብርሃ ደስታ)

June 27, 2014

ከትንሽ ደቂቃዎች በፊት በመቐለ ሰልፍ ጉዳይ ወደ መቐለ ከተማ ከንቲባ ፅሕፈትቤት ሐላፊ ተጠርተን ነበር። “ዝግጅቱ ከጨረስን በኋላ ሊያግዱን ነው እንዴ” በሚል በስጋት ተወጠን እዛው ስንደርስ “አንድ የረሳነው ፎርም አለ፤ ትፈርማላቹ” አሉን። ምንድነው ስንል? “በሰለማዊ ሰልፉ ለሚፈጠር ማንኛውም ችግር ሓላፊነት እንወስዳለን” ብላቹ ፈርሙ አሉን። ፎርሙም አሳዩን። ፎርሙ ሕገመንግስትና የሰለማዊ ሰልፍ አዋጁ የሚፃረር በመንግስት ሳይሆን በገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ የተዘጋጀ መሆኑ ተረዳን። “ለሚፈጠረው ችግር እኛ ሐላፊነት የምንወስድ ፖሊስ የለም እንዴ? ለፖሊስኮ አሳውቀናል!” አልናቸው። “የለም፤ ራሳቹ ሐላፊነት ትወስዳላቹ። ሌሎች ፓርቲዎችም እንደዛ ይፈርማሉ” ሲሉን ግዜ ሰልፉ ለመከልከል ምክንያት እያፈላልጉ እንዳይሆን ብለን ፈረምን። አሁን በሰልፉ ለሚፈጠር ችግር ሐላፊነት ለመውሰድ ፈርመናል። እሺ እንፈርማለን ብለን እስክርቢቶ ስንይዝ የከንቲባው ፅሕፈትቤት ሐላፊ በጣም ደነገጠ። አሃ! “አይፈርሙም” ብለው አስበው ነበር ማለት ነው አልን።

እንግዲህ የራሳቸው ሐላፊነት ለኛ አስረክበውናል። ፀጥታ የማስከበር ስራኮ የፖሊስ ነው። እንዳውም ሁሉም ሐላፊነት ለኛ ቢሰጡን ጥሩ ነበረ። ዉሃ፣ ፍት ህና ነፃነት ማስፈን ይቻል ነበር።

ያው እንግዲህ ፈርመናል። የህወሓት የደህንነት ሰዎች ግን ከተማዋን መልተዋታል። የህዝብ ስሜት እያጠኑ ያሉ ይመስላል። ህዝቡ ግን የሚፈራ አይመስልም።

ቅዳሜ ጥዋት እንገናኝ።

Previous Story

የታላቁን ወር ረመዳን መግባት አስመልክቶ ከታሳሪ ጀግኖቻችን የተላለፈ አጭር የ‹‹እንኳን አደረሳችሁ›› መልእክት – ከድምጻችን ይሰማ

Next Story

ESAT Radio Fri, June 27, 2014

Go toTop