ፖሊስ በሐዋሳ ከተማ በቅስቀሳ ላይ የነበሩ የአንድነት አባላትን በሙሉ አሰረ
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በነገው እለት ማለትም ሰኔ 15/2006 ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ በራሪ ወረቀት በማደል ፤ ፖስተር በመለጠፍና በሞንታርቦ ቅስቀሳ ላይ የነበሩ የአንድነት አባላትን በሙሉ አስሯል፡፡ በሞንታርቦ ቅስቀሳ ላይ የነበሩት የነበሩ የአንድነት ፓርቲ አባላትን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የመሀል ክ/ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት)በነገው እለት በሀዋሳ ሀተማ ለሚያደርገውን ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ፖስተር በመለጠፍ፡በራሪ ወረቀት በማደልና በሞንታርቦ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ የነበሩ የፓርቲው አባላት በፖሊስ ተይዘው በተለያዩ በከተማዋ ፖሊስ ጣቢያዊች የሚገኙ ቢሆንም ማንም እንዳይጠይቃቸው በመደረጉ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ አልተቻለም፡፡የሀዋሳ ከተማ ከተማ ፖሊስ መምርያ የመሀል ክ/ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት ሀላፊ ስማቸውን መግለፅ እንደማይፈልጉና ማንም መጠየቅ እንደማይችል እንዲሁም መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽነርን ስለሁኔታው ለማናገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡
በእስር ላይ የሚገኙት አባላት የሞባይል ስልካቸውን ተቀሙ
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በነገው እለት ማለትም ሰኔ 15/2006 ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ የሚያካሂደውን ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ በቅስቀሳ ላይ እንዳሉ በፖሊስ ተይዘው የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የመሀል ክ/ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት እንዲሁም በባህል አዳራሽ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ የሚገኙ የአንድነት አባላት ከማንም ጋር እንዳይገናኙ የሞባይል ስልካቸውን ተቀሙ፡፡ከስልካቸው በተጨማሪም በራሪ ወረቀቶቻቸውን ፖሊስ በሀይል ቀምተዋል፡፡
\
በአዋሳ ፖሊስ የአንድነት ስራ አስፈፃሚ አባልን አሰረ
****************************************
አንድነት ፓርቲ በአዋሳ ከተማ የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ የፓርቲው ብሄራዊ ምክር ቤት አባልና በአንድነት ፓርቲ የሴቶች ጉዳይ ስራ አስፈፃሚ የሆኑትን ወ/ሪት እልፍነሽ ከበደን የተሳፈሩበትን ሚኒባስ በማስገደድ ወደ ምስራቅ ክ/ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል ፡፡ሀላፊዋ ከጠዋቱ 4፡00 ጀምሮ በጣቢያው ታስረው የሚገኙ ሲሆን በምን ምክንያት ቁጥጥር ስር እንደዋሉና እስከመቼ በእስር እንደሚቆዩ ለማወቅ እንዳልቻሉ ገልፀዋል ፡፡የጣቢያውን ሀላፊ ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ በስብሰባ ምክንያት ሊሳካ አልቻለም