ሚሊዮኖች ድምጽ – የእሪታ ቀን ሰልፍ በሚያዚያ 26 ቀን እንደሚደረግ የአዲስ አበባ አስተዳደሩ እውቅና ሰጠ !

April 17, 2014

«ህግንአክብረንለድርድርየማናቀርበውንህገመንግስታዊመብታችንንአሳልፈንአንሰጥም።ታላቁህዝባዊሰላማዊሰልፍ ‹‹የእሪታቀን ›› በሚልመሪቃልሚያዚያ 26፣2006 ዓ.ምበአዲስአበባከተማይደረጋል፡፡» ሲሉ የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌው ገለጹ።

ፓርቲዉ ከአዲስ አበባ አስተዳደር አስፈላጊዉን እውቅና ያገኘ ሲሆን ፣ ከትንሳኤ በዓል በኋላ በሃያ ሶስቱም የአዲስ አበባ ወረዳዎችና በአዲስ አበባ አካባቢ ባሉ ቦታዎች ቅስቀሳ እንደሚያደርግ ለማወቅ ተችሏል። የአዲስ አበባ ሕዝብ በዚህ ቀን፣ በነቂስ ወጥቶ ድምጹን ያሰማል ተብሎ ይጠበቃል።

ሰልፉ ሊደረግ የታሰበው መጋቢት 28 የነበረ ሲሆን፣ በወቅቱ አስተዳደሩ ሕግን ባልጠበቀ መልኩ፣ አማራጭ ቀን ወይም ቦታ እንዲቀርብ ሳይጠይቅ በደፈናዉ እውቅና አልሰጠም የሚል ደብዳቤ መላኩ ይታወቃል። ለሕገ ወጥ እርምጃ እውቅና አንሰጥም በሚል፣ አንድነት የአስተዳደሩን ደብዳቤ እንደማይቀበል በማሳወቅ፣ የቅስቀሳ ዘመቻ ማድረጉን ፣ ከዚያም ጋር በተገናኘ 4 አባላት በፖሊስ መደብደባቸውን ፣ አምስት ደግሞ ለሳምንት መታሰራቸው ይታወቃል።

አስተዳደሩ የላከዉን ሕገ ወጥ ደብዳቤ በመቀልበስ፣ ለሚያዚያ 26 ቀን 2006 ዓ.ም  በአዲስ አበባ ከተማ ሰልፍ እንዲደረግ እውቅና  እንዲሰጥ መደረጉ ፣ የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች ያደረጉት ትግል ዉጤት እንደሆነም የሚያመላክት ነው።

 

 

Previous Story

የአንበጣ መንጋ በሶማሌ፣ በኦሮሚያና በድሬደዋ ባሉ 13 ወረዳዎች ስጋት ሆኗል

Next Story

[የሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጉዳይ] የአቡነ ማርቆስ ቤተክርስቲያኑን አሳማ አርቡበት ንግግር፣ የካህናቱ አንቀድስም ደብዳቤና የፍርድ ቤት ትዕዛዝ

Go toTop