Millions of voices for freedom – UD
የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት” በሚል መሪቃል በደሴ የተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡ በስፍራው የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ከፍተና አመራሮችና የዞን አመራሮች በሰልፉ ለተሳተፈው የደሴ ህዝብ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ #Dese #UDJ “እድሜ ለአንድነት አስተነፈሰን” የደሴ ነዋሪ. ይህ ሁሉ አልፎ ዛሬ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ በአስተዳደሩ ላይ በተለይም በመሬት ይዞታ ባለቤትነት ጉዳይ እና አላግባብ ስለታሰሩት ኢትዮጵያውያን ድምጹን ከፍ አድርጎ እያሰማ ይገኛል:: ሰላማዊ ሰልፉ እንደተጀመረ ፖሊስ መንገዱን በመዝጋት ሰልፈኛውን ለማወክ ጥረት አድርጎ ነበር:: ህዝቡ ግን ፖሊስን እየጣሰ ሰልፉን በሰላማዊ መንገድ እያደረገ ነው::
የደሴው ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ እየተካሔደ ቢሆንም የአዲስ አበባው ዋና ጽ/ቤት ከፍተኛ በሆነ የፖሊስ ሀይል ተከቧል፡፡
ተቃውሞ ሰልፍ ላይ ከሚስተጋቡ መፈክሮች ውስጥ
– መሬት ለህዝብ ይመለስ
– ጭቆና በቃን
– ድል የህዝብ ነው
– በግፍ የታሰሩ ይፈቱ
– አንድነት ኃይል ነው
– የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ