ወለምታ እና የጡንቻ መሸማቀቅ ሲደርስ መደረግ የሚገባቸው ነጥቦች

July 7, 2011

ደረጃ ሲወጡ፣ ሲሮጡ፣ ከባድ እቃ ሊያነሱ ሲሞክሩ ወይም ሌላ ዓይነት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ በቀላሉ የጡንቻ መሸማቀቅ ሊደርስብዎት ይችላል፡፡ የጡንቻ መሸማቀቅ ማለት በእጅዎ፣ እግርዎ፣ ወይም ጀርባዎ ላይ ባሉ ጡንቻዎ ላይ የሚደርስ ማበጥ፣ መድረቅ ወይም መታመም ነው፡፡ እንደ ጉልበትዎ ፣ ትከሻዎ ክርንዎ ባሉ መገጣጠሚያዎች ላይ የሚደርስ ህመም ከጡንቻ መሸማቀቅ/ ወለምታ ጋር ይመደባል፡፡
በጡንቻ መሸማቀቅ የተጎዳው አካልዎ ላይ ለአንድ ወይም ለሁለት ቀናት ያህል ለ 20 ደቂቃ በረዶ በጨርቅ አድርገው ይይዙና ለሌላ 20 ደቂቃ ደግሞ ያሳርፉታል፡፡ መልሰው ለ 20 ደቂቃ ያህል በረዶውን ያደርጋሉ፡፡ ይህንንም የተቻለዎትን ያህል ጊዜ ይደጋግሙት፡፡ ህመሙ የሚሰማዎት አካልዎንም ያለ ስራ እንዲያርፍ ያድርጉት፡፡  የህመም ማስታገሻ (ፔን ኪለርም) ህመሙን ለማስታገስ ይጠቀሙ፡፡  3 ቀን ቆይተውም የጡንቻ መሸማቀቅ/ ወለምታ የደረሰበት ቦታ እብጠቱ ከቀነሰልዎት በኋላ የሞቀ ውሃ ሙቅ ውሃ መያዣ ላስቲክ በመጠቀም ወይም በአቅራቢያዎ ከሚገኝ መድኃኒት መደብር (ፋርማሲ) ሙቀት የሚሰጥ ተለጣፊ ፓድ ገዝተው ህመሙ በደረሰበት ቦታ ያስቀምጡት (ይለጥፉት)፤ የጡንቻ መሸማቀቅ/ ወለምታ የደረሰበትን ቦታ ብዙ እንዳይነቃነቅ በፋሻ ጠበቅ አድርገው ይሠሩት፡፡ የሚከተሉት ነገሮች ከተከሰቱ ግን ዶክተር/ ሃኪም ጋር መሄድ ይኖርብዎታል፡፡  ትልቅ እብጠት፣ ከባድ ህመም ወይም የቆዳ ጥቁረት ከደረሰብዎት፤  ለመንቀሳቀስ እስኪቸገሩ ድረስ የጡንቻ ህመም ከደረሰብዎት። በነገራችን ላይ በሥራ ቦታ የሚደርሱ ወለምታዎች እና አደጋዎችን ዝም ማለት አይገባንም። በየትኛውም መስሪያ ቤት አደጋ ቢደርስብን ወዲያውኑ የኢንጁሪ ሪፖርት ፎርም መሙላት ይገባል።S

Previous Story

CECAFA Kagame Cup: Salhadin Said of St George on track to retain Golden Boot Award

Next Story

ድምፃዊት ፀደኒያ ገ/ማርቆስ (የመጀመሪያዋ የኮራ አዋርድ አሸናፊ ኢትዮጵያዊት)

Go toTop