(addisneger)ባሳልፍነው ሳምንት አዲስ አበባ የመጡት ሂላሪ ክሊንተን “ሦስት ቀናት ይቆያሉ” ሲባል ኤርትራ በፈነዳው እሳተ ጎመራ ምክንያት ከ8 ሰዓታት ቆይታ በኋላ ድንገት ኢትዮጵያን ለቀው ወጥተዋል፡፡ በቆይታቸው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊን ብቻ ሳይሆን ቱባ የአፍሪካ መሪዎችን ሰብስበው አነጋግረዋል፡፡ ለጋዳፊ ድጋፍ እንዳይሰጡ መሪዎቹን አግባብተዋል፤ ቦትስዋናንና ጋናን ስለ ዲሞክራሲያቸው አሞካሽተዋል፡፡ “አፍሪካ ውስጥ ስለሚያወርሱት ዲሞክራሲ ሳይሆን ስለ ስልጣንና ረዥም ጊዜ ስለ መግዛት አብዝተው የሚጨነቁ መሪዎች በዝተዋል” ሲሉ አቶ መለስንና መሰሎቻቸውን በነገር ሸንቆጥ አድርገዋቸዋል፡፡
ወ/ሮ ሂላሪ በአፍሪካ ኅብረት ተገኝተው ንግግር ሲያደርጉ ታድያ ድንገት መብራት ሄዶ ንግግራቸው ተቋርጧል፡፡ ይህ ክስተት የዝግጅቱን አስተባባሪዎች ክፉኛ ቢያሳፍርም ወይዘሮዋ እንዲህ ብለው ተናገሩ፡- “when things like this happen, you just keep going››፡፡ ፎርቹንና ሌሎች ጥቂት የአገር ቤት ጋዜጦች ዘግበውታል፡፡