በአሲድ የተደፋባት ትግስት ቀብሯ ተፈጸመ

June 11, 2011

በአሰቃቂ ሁኔታ አሲድ ፊቷ ላይ የተደፋባት ወጣት የቀብር ስነ-ስርዓት መፈጸሙን የዘ-ሀበሻ ጋዜጣ ዘጋቢ ከአዲስ አበባ ገለጸ። እንደ ሪፖርተራችን ገለጻ ቁጥሩ ብዛት ያለው ሕዝብ በቀብር ስነስር ዓቱ ላይ በመገኘት ሃዘኑን የገለጸ ሲሆን፤ በቀጣይም የሟችን ሁለት ልጆች በመርዳት ላይ ሕዝቡ ሲያወራ እንደነበር ተናግሯል። በውጭ ያሉ ሰዎችም የሟችን ሁለት ልጆች ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉና መልካም ዜጋ እንዲሆኖ ለማድረግ መረባረብ እንዳለባቸው ከአዲስ አበባ የደረሱን አስተያየቶች ጠቁመዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሟች ትግ እስት ጉዳይ የአዲስ አበባ ጋዜጦችን እና መጽሄቶችን ከፍተኛ ሽፋን ማግኘቱ ታውቋል። በዚህም መሠረት ቅዳሜ በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ስለትግስት መኮንን ሞት የሚከተለውን ጽፏል። ለውድ አንባቢዎቻችንና ጋዜጣውን ማግኘት ለማይችሉ ስካን አድርገን አቅርበናል። ይመልከቱት፦

Previous Story

ከ10 በላይ ኢትዮጵያዊያን በየመን ጦርነት ሞትና ያሳደረው ስሜት…!!!

Next Story

Ethiopia to buy more than 200 T-72 tanks from Ukraine for $100 million

Go toTop