ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋን የት አደረሱት⁉️

April 17, 2023

ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ ማን ነው በትንሹ? ፦ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ ማለት እንደ አሁን ዘመኑ ካድሬዎችና ባለ ጊዜዎች ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቅጡ ሳያጠናቅቁ ዶ/ር ፣ባለ ማስተር ፣ባለ ድግሪ እንደሚባሉት ቤት ተቅመጥው የትምህርት ማስረጃ ሰርተፊኬት እንደሚቀበሉ የጠረባ ዶክተሮች ፣ባለ ማስተሮች እና ባለ ድግሪዎች ወዘተ አይደለም ።

ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ የቀድሞ የጎንደር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአሁኑ የጎንደር ዩኒቨርስቲ የህክምና ፋክልቲ በአገር ደረጃ በመቶዎች የተመረጡ ፣ብቁ እና ምጡቅ አእምሮ ያላቸው ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ በሚቀላቀሉበት ዘመን ፤ከእከሌ ት/ቤት እኮ እከሌ ብቻ አለፈ በሚባልበት ከጥቂቶች የተመረጡና ብቁ ሁነው ከተገኙ ተማሪዎች አንዱ በመሆን ፤በተጠቀሰው የህክምና ኮሌጅ የመጀመሪያ ዲግሪውን (በህክምና ዶክተር ) በከፍተኛ ብቃት ያጠናቀቀ ምርጥ ሀኪም ነው ። በመቀጠልም በተለያዩ አለም አቀፍ ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች በምጣኔ ሀብት ፣በስትራቴጂ ፕላኒንግ ወዘተ ዓለም አቀፍ የሆነ ዕውቀትን የሸመተ፤ዓለም አቀፍ ተዋዳዳሪ የሆነ የአማራ ምሁር ነው ።

የቀድሞው ኢህዴግ ይህንን ዓለም አቀፍ ዕውቀቱን በመፈለግ ከእኛ ጋር ስራ ከፍተኛ ጉትጎታና ልመና ፤ካድሬ ሁንና ከፍተኛ ስልጣን እንስጥህ ቢሉትም፤ምሁር ጠል እንደሆኑ ስለሚያውቅ አልቀበልም በማለት ለህሊናው ታማኝ በመሆን ላለፉት በርካታ አመታት በአገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ተቋማት የሰራ ብቃት ያለው የአማራ ምሁር ነው ።

ስርዓተ መንግስቱ በሁለቱም ኢህዲጎች ምሁር ጠል (በተለይም አማራዊ ምሁር ጠል ) በመሆኑ እንደዚህ አይነት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ዕውቀት ያላቸውን ምሁራን ያሳድዳል ፣ከስራቸው ያፈናቅላል ፣ያስራል እንዲሁም ይገድላል ።

ከዚህ ላይ እንደ አብነት ማንሳት የሚቻለው ፦ከአርባ በላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ምሁራን ላይ በያኔው ጠ/ሚ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ከአ/አ ዩኒቨርስቲ የተባረሩ ምሁራን ፤ አንጋፋው ፣እውቁ የልብ ስፔሻሊስት ሃኪሙ ፤የአማራው ፈርጥ እና አብሪ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ በግፍ አስሮ መግደል ወዘተ ላይ የተፈፀመውን ምሁር ጠል ተግባራት ማስታወስ በቂ ነው ።

ለስርዓቱ የገበሩትን ፣ያደሩትን ምሁራዊ ካባቸውን አስውልቀው የመንግስታዊ ቡድኑ አፈ ቀላጤ ፣ተላላኪ ፣ሎሌ እና የፀረ ምሁር መንግስታዊ ስርዐቱ አሳላጭ እንዲሁም በምሁር ስም ህዝብ አደንቋሪ ፣አሳሳች እና ተንታኝ ያደርጋቸዋል ።

ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ ይህ የአማራ ተወላጆችን የሚሳድደው ፣የሚያስረው እና የሚገድለው የስርዐቱ አፋኝ ቡድን ሃሙስ ዕለት ከምሽቱ 4:00 ሰዐት ላይ መደበኛ ህይወቱንና እንቅስቃሴውን እያከናወነ ባለበት ወቅት ከ50 በላይ ቀይ ቦኔት የለበሱ ኮማንዶዎች አፈና ፈፅመውበታል ።እስካሁንም የት እንዳለ አይታወቅም ።
ከዚህ ቀደም ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ በባህር ዳር ሰባታሚት ማረሚያ ቤት “መፈንቅለ መንግሰት ለማድረግ ሲያሴሩ ” አገኘኃቸው በማለት ከአስራ አራቱ (14) የአማራ ፋኖ አንድነት አመቻቾች ጋር ከሁለት ወር በላይ ታስሮ እያንዳንዳቸው በ25ሺ ብር ዋስ መለቀቃቸው ይታወሳል ።

የአማራ ወጣቶች ማህበር ይህ መንግስታዊ አፋኝ ቡድን የሚያደርገውን ሁሉን አቀፍ አፈና ፣ደብዛ ማጥፋት እንዲያቆም ጥሪያችን እናስተላልፋለን ።በተጨማሪም ከዚህ ቀደም አፍኖ ያሰራቸውን የአማራ ምሁራን፦ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው ፕሮፌሰር ማዕረጉ ፣መምህር ሄኖክ ፤መምህርት ፣ጋዜጠኛ እና ፀሐፊ መስከረም አበራ ፤የአማራ ወጣቶች ማህበር ስራ አስፈፃሚ ሰለሞን ልመንህ ወዘተ ፣ጋዜጠኞች እና ማህበራዊ አንቂዎች እንዲሁም የታሪክ ምሁሩ ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቃቸው እናሳስባለን ።

በማሰር ፣በማዋከብ እና በማሳደድ የሚቆም ፥የተጀመረ ትግል የለም ።የትግላችን መዳረሻ የአማራ ህዝብ ነፃነት ነው ።

ላንጨርስ የጀመርነው ትግል የለም‼️

 

ማራ ሚዲያ ማዕከል

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ጉዞ ወደ ኢትዮጵያ ትንሣኤ! -nሲና  ዘ ሙሴ

Next Story

ለተፈናቃዮች ሀገራቸው የት ነው?

Go toTop