የአብይ የጤና ሁኔታ ይመርመር

March 24, 2023

ሀገር ምራ ብለው ቢሰጡት አደራ፣
በከፍታ እንዲቆም ላአንድ ሀገር ባንዲራ፣
ዝቅ ብሎ ቀረ እጎሰኞች ተራ፣
በደም ተለውሶ በህዝብ መከራ፣፣
ከባለፉት ሁለት ወራት ጀምሮ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የማይሆኑ እና የኢትዮጵያን እጅግ የሚያስቆጡ ውሳኔዎችን እየወሰኑ እያደረጉ ነው፡፡ ምናልባት ጠቅላይ ሚንስትሩ ቀስ እያለ በሚጎዳ እና አእምሮን በሚያስት በራዳዮ አክቲቭ ንጥረ ነገር ተመርዘው ሊሆን ስለሚችል ከፍተኛ ሕክምና ወዳለበት ቦታ ተወስደው እንዲታከሙ እና የዕለት ተዕለት የመንግስት ተግባራትን የሚያከናውን ጊዜያዊ ሌላ ጠቅላይ ሚንስትር እንዲሾም ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም የሚመለከታችሁ የመንግስት አካላት ሁሉ የሚጠበቅባችሁን ኃላፊነት እንድትወጡ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ የጠ ቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ችፍ ኦፍ ስታፍ፣ የፕሮቶኮል ሹሙ፣ የቤተ መንግስት ጠባቂዎች እና የሪፐብሊካን ጋርድ አባላት፣ የሚንስትሮች ም/ቤት፣ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባት የሚጠበቅባችሁን እና በሕግ የተጣለባችሁን ኃላፊነት እንድትወጡ አጥብቀን እናሳስባለን፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር እና በሀገር እና በሕዝብ ላይ ተጨማሪ በደል ቢደርስ ሙሉ ኃላፊነት እንደምትወስዱ ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን፡፡

ጠቅላይ ሚንስትሩ ከፍተኛ የጤና መታወክ ላይ ነው ያለው፡፡ የመታከም መብት አለው፡፡ ለእርሱ ላይታወቀው ይችላል፡፡ ስለዚህ በቅርቡ ያላችሁ ሰዎች ልታሳክሙት ይገባል፡፡ ወደ ሙሉ ጤነኝነቱ እስኪመለስም ድረስ በምትኩ ሌላ ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚንስትር ልትመርጡ እና ሀገራችሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ ከአደጋ ልትታደጓት ይገባል፡፡ የሀገር መከላክያ ሰራዊት እና የፌደራል ፖሊስ አባላት ከመቼውም ጊዜ በላይ በውጭም በውስጥም ከሚጣልባት አደጋ ሀገራችሁን ልትከላከሉ እና ልትጠብቁ ይገባል፡፡

 

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ
Anonymous

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

አብይን ለመቀበል ዝግጅት እየተደረገ ነው ተባለ | ግርማ የሺጥላ የሰጡት ማሳሰቢያ

Next Story

ጆከሩን መዘው ፖለቲካዊ የፖከር ካርታ ጫዎታውን ጠቅላዩ አሥጀምረዋል – ሲና ዘ ሙሴ

Go toTop