“በመንግስት ጫና በአባልነትም ሆነ በአመራርነት መስራት የማልችልበት ደረጃ ላይ ደርሻለሁ” እስክንድር ነጋ

August 10, 2022

የባልደራስ ፕሬዝደንት አቶ እስክንድር ነጋ ሀምሌ 16፣2014 ዓመተ ምህረት ካሉበት ቦታ በጻፉት ደብዳቤ፣ ተረኛና ጨቋኝ መንግስት በፈጠረው ጫና ሳቢያ በፓርቲያቸው በአመራርነትም ሆነ በአባልነት መስራት የማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ይፋ አደረጉ። የደብዳቤያቸው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል። ፊርማቸው ያረፈበት የአጅ ጽሁፋቸውም ከዚህ ደብዳቤ ጋር ተያይዟል።

ሀምሌ 16፣ 2014

ለባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ

ኢትዮጵያ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንድትሻገር ለዓመታት የበኩሌን አስተዋጽዖ ሳደርግ መቆየቴ ይታወሳል። በአሁኑ ጊዜ ግን፣ ተረኛው ጨቋኝ መንግስት በባልደራስም ሆነ በሃገር አቀፍ ደረጃ በፈጠረው የለየለት አምባገነናዊ ጫና ሳቢያ፣ በአባልነትም ሆነ በአመራርነት መስራት የማልችልበት ደረጃ ላይ ደርሻለሁ።

በመሆኑም የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፣ አባላት፣ በየደረጃው ያሉ የፓርቲው አመራር አባላት፣ መላ አባላትና ደጋፊዎች፣ እንዲሁም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ከፓርቲው ምክትል ፕሬዝደንት አቶ አምሃ ዳኘው ጋር ሙሉ ለሙሉ በመተባበር ስራቸው የተቃና እንዲሆን እንድትተባበሯቸው በትህትና እጠይቃለሁ።

በመጨረሻም፣ እቅድ የተያዘለት የባልደራስ ጠቅላላ ጉባኤ በተሳካ ዝግጅት እንዲከናወን ያለኝን ብርቱ ተስፋ እየገለጽኩ፣ ባልደራስ በሃገር አቀፍ ፓርቲነት አድጎ የማየት ተስፋችን ወደ ተግባር ተተርጉሞ ለማየት የፈጣሪ መልካም ፈቃድ ይሁን።

ከሰላምታ ጋር

እስክንድር ነጋ

ባልደራስ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ጉራጌ ለምን ክልል መሆን አስፈለገው? (ይርጋዓለም ብርሃኑ እንደጻፈው)

Next Story

ሕዝብ የአስተዳደር ውሳኔን የመቀበል ግዴታ የሚኖርበት እንደ ዜጋ ሂደቱ ላይ የመሳተፍ እና የማወቅ መብቱ በአግባቡ ሲከበርለት ብቻ ነው!

Go toTop