በደቡብ ወሎ ቃሉ ወረዳ የአብን የወረዳ አመራር አባል መታሰሩ ተገለፀ!

July 8, 2022

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የቃሉ ወረዳ አመራር አባልና የተወካዮች ምክር ቤት እጩ የነበረው አቶ አብደላ መሐመድ በትናንትናው እለት በመንግሥት የፀጥታ አካላት ከቤቱ ተይዞ መታሰሩ ተገለፀ፡፡

አቶ አብደላ መሐመድ በሀርቡ ከተማ ነዋሪና በሰላማዊ መንገድ የሚታገል ፥ የረዥም አመታት የትግል ተሳትፎ የነበረው አባላችን ሲሆን በቅርቡ “ህግ-ማስከበር” በሚል ሽፋን በተጀመረው የዘመቻ አፈና ተረጋግቶ መኖርና ወጥቶ መግባት እስከሚቸገር ድረስ ፥ ቤቱን ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ከመበርበር ጀምሮ ክትትልና ማሳደድ እየተፈፀመበት በመቸገሩ ፥ አካባቢውን ጭምር ለቆ እስከመሰደድ ደርሷል፡፡ ሆኖም ከ3 ቀን በፊት ወደቤቱ ሲመለስ የመንግሥት የፀጥታ አካላት ከመኖሪያ ቤቱ ይዘው ለእስር እንደዳረጉት ለማወቅ ተችሏል!

“ህግ-ማስከበር” በሚል ሽፋን ባለፉት ወራት በተጀመረው መንግስታዊ የጅምላ አፈና ፥ በተለያዩ አካባቢዎች በርካታ የንቅናቄአችን አመራርና አባላት ፥ ህጋዊ ስርአትን እንኳ ባልተከተለ መልኩ ለአፈና የተዳረጉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ በአሁኑ ሠአት ያሉበት የማይታወቁና በህጉ አግባብ ፍርድ ቤት ያልቀረቡ እንደሚገኙበት የሚታወስ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ወዴት ? እንዴት ? ነው፤ የጠ/ሚሩ አካሄድ ? አልገባኝም – ሲና ዘ ሙሴ

Next Story

1443ኛው የኢድ አል አድሀ ዐረፋ በዓል በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው – ኢድ ሙባረክ! ሰላም ፣ ፍቅር ፣ አንድነት!

Go toTop