ንፁህ የአማራ ደም ወለጋ ተንጣሎ፣
ጠራርጎ ሊወስደው ዓባይ መጣ ደሞ፣
የተከሉት ችግኝ ስላልዋጠው መጦ፡፡
የደም ጅረት ሲፈስ ፀጥና እረጭ ያሉ፣
የዓባይ ጎርፍ ሲባል መብረቅ ይሆናሉ፡፡
የአስከሬን ተራራን ተመጤፍ ያልጣፉ፣
ምሁር ተብዮዎች ግድብ ይዘክራሉ፡፡
የአስራ አምስት ቀን ህፃን ተደፍታ ስታለቅስ፣
ተናቶች ታያቶች የሬሳ ክምር ውስጥ፣
ምኑን ሰው ሆንና ቆመን የምንሄድ፡፡
ኧረ ተው የሰው ልጅ በሰውነት ቀጥል፣
ተበግ መንጋ አትውረድ በአባይ በመደለል፡፡
በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)
ሰኔ ሁለት ሺ አስራ አራት ዓ.ም.