አንጋፋውን ጋዜጠኛና ደራሲ ዜናነህ መኮንን እንድረስለት

May 4, 2022

https://www.gofundme.com/f/support-tk-show-and-hiber-radio?utm_source=customer&utm_medium=copy_link&utm_campaign=p_cf+share-flow-1

‹‹አንተ ከአገርህ ልትወጣ ትችላለህ። አገር ግን ካንተ ውስጥ አትወጣም! … እናም ኢትዮጵያ፤ አገሬ ሳልገባ አምላክ አይግደለኝ! ›› – ጋዜጠኛና ደራሲ ዜናነህ መኮንን
አንጋፋው ጋዜጠኛና ደራሲ ዜናነህ መኮንን ባለፉት ሶስት ዓመታት ሁለቱም ኩላሊቶቹ ሥራ በማቆማቸው በሚኖርበት እስራኤል እየሩሳሌም በአስቸጋሪ ሁኔታ ሕክምናውን ሲከታተል ቆይቶዋል፡፡ በዚህ ሁሉ ጊዜ ከሕመሙ እየታገለነ በሳምንት ሶስት ቀን አድካሚውን የኩላሊት እጥበት ሲያካሂድ በራሱ እና በቤተሰቡ ሁሉን አፍኖ ቆይቶዋል፡፡ በሙያውና በልምዱ አገሩንና ወገኑን አስመልክቶ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ላይ ሕብር ሬዲዮን ጨምሮ እየቀረበ አስተያየቱን በመስጠት ዛሬም አገሬን ወገኔን ኢትዮጵያን ብሎ የተሻለ ቀን እንዲመጣ ትላንትን ከዛሬ እያጣቀሰ ይተነትናል፡፡ያሳስባል፡፡ይመክራል፡፡ በዚህ ሁሉ መሀል ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ የጤናው ሁኔታ እያሳሰበው የተሻለ ሕክምና ማግኘትን አስቦ በተስፋ ብቻውን ታግሎዋል፡፡ ከተሳካለትም የኩላሊት ንቅለ ተከላ ለማግኘት እየጣረ ነው፡፡ ዛሬ የእኛን ድጋፍ ይፈልጋል፡፡
አንጋፋው ጋዜጠኛና ደራሲ ዜናነህ መኮንን ትላንት በአገር ቤት በኢትዮጵያ ቴሌቪዝን እና ኢትዮጵያ ሬዲዮ ዜና አንባቢነቱ ብቻ ሳይሆን ዛሬም አሰገምጋሚ ድምጹን የጀርመን ድምጽ (DW Amharic) የጣቢያ መክፈቻና መዝጊያ ላይ ‹‹ይህ ዶቸ ቬሌ ነው፡፡ ዶቸ ቬሌ ከመሐል አውሮፓ በየዕለቱ የሚያሠራጨውን ዝግጅት ማሰማት ይጀምራል፡፡ >> ሲሉ ይሰሙታል፡፡ ከአገሩ የወጣው በ1984 ዓ.ም. ሲሆን በጀርመን ድምጸና በኢያው እስራኤል በሚገኝ የአማርኛ ራዲዮና ቴሌቪዥን ታቢያም ለተወሰኑ ጊዜያት አገልግሎዋል፡፡ በደራሲነቱም ያበረከታቸው መጽሐፍት ነፃነት የተሰኘው በአምስት ዓመቱ የጣሊያን ጦርነት የኢትዮጵያ ጀግኖች የከፈሉትን መስዋዕትነት የሚዘክር ታሪካዊ ልቦለድ ነበር እና ከጣራው ሥር የተሰኘው ባማህበራዊ ሕይወት ላይ የሚያጠነጥን በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተጻፈ የልቦለድ ሥራው ነው፡፡ ‹‹በረከተ መርገም››ን የሚሞግት) ‹‹በረከተ ራዕይ›› በሚል ርዕስ የግጥም ሲዲ በ1999ዓ.ም አውጥቷል፡፡
በረከተ ራዕይ ተስፋን – ነግን ለማየት እንድንታትር የሚያመላክት ‹‹መልዕክተኛ›› ሥራው ነው፡፡ ዜናነህ በሙያው ‹‹ትላልቆቹ›› ዘንድ ትልቅ ከበሬታ ያገኘ ሰው ነው፡፡ አብዬ መንግሥቱ ለማ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ሲያስተምሩ ‹‹ዜና ዜናነህ አነበበ ሲባል – ዘመዳዊ ተሳቢ ነው›› እያሉ ስሙን ይጠሩ ነበር፡፡
* በ1967ዓ.ም በማስታወቂያ መምሪያ ጋዜጠኝነት የጀመረው ዜናነህ በ1970ዓ.ም ሙያው ለእሥር ዳርጎታል፡፡ ከፍተኛ አንድ – ማዕከላዊ ከዚያም ዓለም በቃኝ ድረስ እሥር ቤቶቹን አፈራርቋል፡፡
* ጋዜጠኛና ደራሲ ዜናነህ መኮንን የሦስት ሴት ልጆች አባት ነው፤ ቢታንያ(28) – ነፃነት(25) – ከፈረንጅ የተወለደችው ሩኒያ(18) ናቸው፡፡
የሕክምና ትግሉን በገንዘብ እንድንደግፈው ለወገኖቹ ጥሪ አቅርቦዋል፡፡ እባካችሁ ዝንጋፋውን ጋዜጠኛና ደራሲ ዜናነህ መኮንን እንድረስለት ስንል በአክብሮት ጥሪ እናቀርባለን፡፡ ልባችሁ የፈቀደውን ስትለግሱ ቲፕ የሚለውን 0.00 አድርጋችሁ ማለፍ ትችላላችሁ፡፡
ይህን መልዕክት ሼር በማድረግ ሌሎችም መረጃውን እንዲያገኙ ያድርጉ፡፡እናመሰግናለን

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ያንቀላፋ የሚመስለው ጽንፈኛው የውሃቢው ቡድን” ሰበብ የማሽተት ሱሱ  ተነስቶበት  “ፋኖ ይውደም “ ፋኖ ሌባ” ማለት ጀምሯል! – ጌታቸው ረዳ

Next Story

የኢዜማ መኢሶናዊ ጉዞ – በኡመር ሽፋው

Go toTop