አዲስ የተሾሙት አምባሳደር ስለሺ በቀለ ዋሽንግተን ዲሲ ገቡ

May 1, 2022
በአሜሪካ የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ስለሺ በቀለ ዋሽንግተን ዲሲ ገብተዋል።
አምባሳደር ስለሺ በዳላስ አለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲዲርሱ የኤምባሲው ባልደረቦች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በአሜሪካ ቆይታቸው የሁለቱ አገራት ግንኙነት የበለጠ እንዲሻሻል አበክረው እንደሚሰሩም አምባሳደር ስለሺ ገልፀዋል።
በተመደቡበት የስራ ኃላፊነት የበለጠ ስኬት እንዲገጥማቸው የሚሲዮኑ ባልደረቦች መልካም ምኞታቸውን ገልጸውላቸዋል።
አምባሳደሩ በሚያደርጓቸው የስራ መሳካት በበለጠ ተነሳሽነትና የሀገር ፍቅር ከጎናቸው እንደሚቆሙ ቃል ገብተዋል።
ላለፉት ሦስት ዓመታት በአሜሪካ የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ላገለገሉት ለአምባሳደር ፍጹም አረጋ በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባልደረቦች ሽኝት አድርገውላቸዋል።
አምባሳደር ፍጹም በአሜሪካ ቆይታቸው ለተገኙ ውጤቶች ከጎናቸው ለነበሩ ቤተሰቦቻቸውና የስራ ባልደረቦቻቸው ምስጋና ማቅረባቸውን ኢፕድ ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
(ኢ ፕ ድ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የሀጂ ሙፍቲ መልእክት

Next Story

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ታሰረ።

Go toTop