በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ፊርማ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሆኜ በመመደቤ አንዳንድ ሰወች ቀደም ብየ የታገልኩትንና ሌቦችን ያጋለጥኩበትን ትግል በጠቅላይ ሚኒስትሩ ታዝዤ እና መጠረግ የነበረባቸውን ሰዎች ለማሰጠረግ የፈፀምኩት ተግባር አድርገው መመልከታቸው አሳዛኝ ነው።
መርህ እንዲከበር ያደረግኩትን ትግል የሴራ አካል ማድረግ ሌሎች ታጋዮች እንዳይፈጠሩ እና ሌቦችና ሙሰኞች እንዲበረታቱ በር የሚከፍት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ በፊት እንደነበሩት መሪወች ነቀፋዬን ችላ ከማለት እና በእኔ ላይም የበቀል እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ የህግና የመርህ ማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ ማድረጋቸው በበጎ የሚታይ ለውጥ ነው። ከዚህ ውጭ የእኔን ነቀፋ ከመጥፎ አተያይ ከማየት ይልቅ በበጎ ወስደውት የበለጠ የሚያበረታታ የኃላፊነት ቦታ ላይ መመደቤ ሌሎች ጓዶችም በየዘርፉ ሌብነትንና ሙስናን እንዲታገሉ የሚያበረታታ ነው።