የአማራ ብልፅግና አመራሮች ስብሰባቸው ላይ ተናገሩ ከተባለው!

March 9, 2022

ባህርዳር:- የካቲት 30/2014 ዓ.ም
አሻራ ሚዲያ

  1. አቶ ፀጋ አራጌ

እኔ በስብሰባዉ ላይ አልተጠራሁም፤በወልቃይት እና በራያ ጉዳይ የምንደራደር ከሆነ በምን አይነት መንገድ ነዉ ከአማራ ህዝብ ጋር ልንገናኝ የምንችለዉ፡፡ እኔ ከዚህ ደም ንፁህ ነኝ፤ እጀንም ከዚህ አላስገባም፡፡ድርድሩስ ቢጀመር ከምን አንፃር ነዉ፡፡ ህወሀት ገና ስጋት በሆነበት ሁኔታ ድርድሩ እንዴት ነዉ፤ ለዛዉም ራያን እና ወልቃይትን አስይዘን፡፡ ጠቅለላይ ሚንስትሩም እንደ አንተ ስራ ቢሆን ኖሮ በዚህ ስብሰበ ላይ አትገኝም ነበር፤እኛ ስለሆን እና ዲሞክራሲ ስላለን እንጅ፤ጦርነቱ እኮ ለኦሮሚያ ስጋት አልነበረም ምክንያቱ ደግሞ ኦሮሚያ ከጦርነት ቀጠና በጣም ሩቅ ስለሆነ እና እንዲሁም ጦርነት አልፎ ቢመጣም ከስላሳ ሽህ በላይ የሰለጠነ ሃይል አለዉ፤በዚህም ዋና የጦርነቱ የስጋት ቀጠና አማራ ክልል ስለሆነ ለእናንት ምንም ነዉ፡፡እኔ እናንተን የመጣል ግዴታ የለብኝም ስራዬን ግን እሰራለሁ ሲሉ ጠንከር ያለ አቋም እንስተዋል፡፡

  1. አቶ ቀለምወርቅ ምህረቴ

ህወሀት ቀድሞም ቢሆን ተደቁሷል፤ደቋል፤ዱቄት ሆኗል ተበትኗል፤እየተባለ ይህንን ያክል በአማራ ላይ ጉዳት ሲያደርስ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት ምን እየሰራ ነበር፡፡ከነመኖሩም እጠራጠራለሁ፡፡የነስብሀት ነጋ መፈታትም የሚያሳየዉ የመንግስትን ድክመትና መንኮታኮት ነዉ ብለዋል፡፡

  1. አቶ ዣንጥራር አባይ

በህወሀት ኢህዴግ ዘመን ዜጎች አረንጓዴ፤ቢጫ እና ቀዩን ሰንደቅ አላማ ይዘዉ ሲወጡ ይታሰሩ እና ይገደሉ ነበር፡፡ይህ አሁንም በብልፅግናም ቀጥሏል፡፡ አረንጓዴ፤ቢጫ እና ቀዩን ሰንደቅ አላማ ከሚይዙት ሰዎች ጋርም ተገናኝታችኋል እየተባልን እየተገመገምንና እየተተቸን ነዉ ሲሉ ጠንከር ያለ ሀሳብ አንስተዋል፡፡

  1. አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

“በቀረችኝ የህይወት ዘመኔ ህዝቤን ለዳግም ባርነት አልዳርግም! ፋኖ ትጥቅ ይፍታ የሚለውን የብልፅግናን አካሄድ አጥብቄ እቃወማለሁ:: ፋኖ የሀገር ዳር ደንበር ዘብ እንጅ የአሸባሪ ተግባር የሚፈፅም ቡድን አይደለም! ሁሉም አማራ ደግሞ ፋኖ ነው”

የአማራ ህዝብ ሊድን የሚችለው በራሱና በእራሱ ብቻ ነው::

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

አዲስ አበባ ሌላዋ የዘመናችን የኢትዮጵያ ወልቃይት! – ፊልጶስ

Next Story

“ጊዜና ትውልድ ገና የሚያከብረው ኢትዮጵያዊ” ገዱ አንዳርጋቸው!!

Go toTop