ብልጽግና ታሟል …ጄኔራል ባጫ ደበሌ እና ጄኔራል ሃሰን ኢብራሂም ከአዋጊ ወደ አምባሳደርነት

January 26, 2022
ከ2ሳምንት በፊት ሙሉ የጄኔራልነት ማዕረግ የተሰጣቸውን ጄኔራል ባጫ ደበሌ እና ጄኔራል ሃሰን ኢብራሂም ከአዋጊ ወደ አምባሳደርነት እንዴው በምን መስፈርትና ሳይንስ ነው 360 ድግሪ የተከረበተው??
አንዲት ሀገር እኮ አንድ የጦር ጀነራል ለማፍራት እና ጀኔራል ለማድረስ እስከ 40 አመት ኢንቨስት ማድረግ አለባት ብለው በአንደበታቸው ከነገሩን 2 ሳምንት እንኳን አልሞላውም….።
አምባሳደር ለመሆን ደግሞ ዓለማቀፋዊ የዲፕሎማሲና የፖለቲካ እውቀትና ክህሎትን ይጠይቃል…።
እንዴት ትናንት የሙሉ ጀነራልነት ማዕረግ ሹሞ በሥራ ላይ ያሉ የጦር ጀነራሎችን ዛሬ ከካበተ ሙያና ሥራቸው ገሸሽ ተደርጎ ምንም እውቀትም ሆነ ልምድ ወደሌላቸው አምባሳደርነት ይሾማሉ
ያሳዝናል ወያኔ/ኢህአዴግ የሚባል መርገምት ሥልጣን ላይ ከተቆናጠጠ ጀምሮ ኢትዮጵያ ታሪኳን እና ክብሯን የሚመጥን እንዲሁም ተለዋዋጭ እና ውስብስብ የዓለም አቀፍ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴና ነባራዊ ሁኔታዎችን ነቅቶ የሚከታተል፥ ለኢትዮጵያ ህዝቧ ሁሌም በተጠንቀቅ የሚቆምና የሚሟገት የሠለጠነ ባለሙያ ለአምባሳደርነት በቅቶ አያውቅም፤ አምባሳደርነት ከነ አክሊሉ ሃብተወልድ ጋር ወደ መቃብር ከወረደ ሰንበትበት ብሏል…።
የንጹሀን ግድያ፣መፈናቀልና እልቂትም ሊነጋ ሲል ይጨልማል ሆኖ ነው ለብልጽግና ጊዜ ይሰጠው፤ ልዩልዩ የአገልግሎት ቦታዎች በሚመጥነው ባለሙያ እየተተኩ( The Right Person on the right Position) ስራናሰራተኛ እየተገናኘ፣ተቋማዊ ሪፎርም እየተደረገ ሀገራችንም ህዝባችንም የለውጥ አመራር ተቋዳሽ ይሆናል ብለን ተስፋ ስናደርግ፤ ጭራሽ ከወያኔው ዘመን ብሶ አረፈው?!ይቺ ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም ከማለት ውጭ ምን እንላለን….!!!
መጥኔ ለሃገሬ….
ይሁን መቸም የፈለገው ቢሆን ወያኔ በስንት ጣሟ አልልም…።

አፈትላኪ ዜናዎች


ጀነራል ባጫ ደበሌን እና ዶ/ር ስለሺ በቀለን ጨምሮ 27 ግለሰቦች በአምባሳደርነት ተሹመዋል። በዚህም መሠረት፡-

1/ አቶ ተፈራ ደርበው
2/ አቶ ደሴ ዳልኬ
3/ ዶክተር ስለሺ በቀለ
4/ ጄኔራል ባጫ ደበሌ
5/ ጄኔራል ሀሰን ኢብራሂም
6/ ወ/ሮ ሽትዬ ምናለ
7/ ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ
8/ አቶ ረሻድ መሀመድ
9/ አምባሳደር ጀማል በከር
10/ አቶ ፈይሰል ኦሊይ
11/ አቶ ኢሳያስ ጎታ
12/ አቶ ፀጋአብ ክበበው
13/ አቶ ጣፋ ቱሉ
14/ ደክተር ገነት ተሾመ
15/ አቶ ዳባ ደበሌ
16/ አቶ ፍቃዱ በየነ
የባሉሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት
እንዲሁም:
1/ አቶ አሳየ አለማየሁ
2/ አቶ ኃይላይ ብርሃነ
3/ አቶ አወል ወግሪስ
4/ ወ/ሮ ብዙነሽ መሠረት
5/ አቶ አንተነህ ታሪኩ
6/ አቶ አክሊሉ ከበደ
7/ አቶ ሰይድ መሐመድ
8/ አቶ ዮሴፍ ካሳዬ
9/ አቶ ዘላለም ብርሃን
1ዐ/ ወ/ሮ ፍርቱና ዲባኮ
11/ አቶ ወርቃለማሁ ደሰታ
በአምባሳደርነት የተሾሙ መሆኑን ከፕሬዝዳንት ፅሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የሚኒስትሮች ምክር ቤት 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ውሳኔ

Next Story

ዐብይ አህመድ፡ በማንነቱ ምክኒያት እኩይ አዟሪት ውስጥ የገባ የወያኔና የኦነግ ድቃይ አውሬ – መስፍን አረጋ

Go toTop