በአፋር ክልል የሚገኙት መጋሌ እና አብአላ የተባሉ አካቢዎች በትግራይ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር መግባታቸውን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ

January 24, 2022

የአፋር የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ጋአስ አሕመድ የአብአላ ከተማ ህወሓት በሚመራቸው ታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር መግባቱን መረጃ እንደደረሳቸው ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።
የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዛሬ ሰኞ ባወጣው መግለጫ ኪልበቲ በተባለው ዞን አብአላ እና መጋሌ ወረዳዎች በኩል ህወሓት ጦርነት እንደከፈተ ገልጿል። የአፋር ክልላዊ መንግሥት በከባድ መሣሪያ የታገዘ ባለው እና በአብአላ፣ በመጋሌ እና በበራህሌ በኩል በሚካሔደው ጦርነት “በርካታ ንፁሀን” መጎዳታቸውን በፌስቡክ ባሰራጨው መግለጫ አስታውቋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ጦርነት ማቆሙን ካሳወቀ ጀምሮ ቂልበቲ ረሱ ተብሎ በሚጠራው ዞን ሁለት አካባቢ በሶስት ወረዳዎች ጦርነት ሲካሔድ እንደቆየ የአፋር የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ጋአስ አሕመድ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። አቶ ጋአስ የአብአላ ከተማ በዛሬው ዕለት በትግራይ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር መግባታቸውን የሚጠቁም መረጃ እንደደረሳቸውም ገልጸዋል። እስካሁን ድረስ በህወሓት ተያዘ ስለተባለው አባላም ሆነ ስለደረሰው ጉዳት የኢትዪጵያ መንግሥት የሰጠው መግለጫ የለም።
የቪዲዮ ዘገባ፦ ሰለሞን ሙጬ
DW

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ሞሳድ የበላው ነጭ ድመት – ሱሌማን አብደላ

Next Story

ኢትዮጵያዊነትን በመንቀል ከኃዲነትን መትከል ምን ይባላል  – ማላጂ

Go toTop