ወሬኛና አስመሳይ፣ ፈሪና አሻጥረኛ ፊልድ ማራሻል ወዘተ እየተባለ አንዳንዶች ሹመቶች ሲሰጣቸው አይተናል

January 10, 2022
ጀግኖች እነ ማን እንደሆኑ፣ ማን ምን እንዳደረገ ሕዝብ ያውቃል። ለጀግና ዕውቅናም ሆነ ሽልማቱ የሕዝብ ክብር ነው!! ብ/ጀኔራል ሻምበል በየነ – ባለከዘራው የነ ዶር አብይ ሽልማት አያስፈልገው። ሕዝብ ያከበረው በልቡ የሸለመው የመከላከያ መኮንን አባል ነው።
“ጀግና ሞትን የማይፈራ ነው”
ደራሲ ብርሃኑ ዘሪሁን
ኢትዮጵያ ስለክብሯ ሞትን የናቁ ልጆች ስላሏት እዚህ ደርሳለች። ኢትዮጵያ በዐቢይ አህመድ ሞልቃቃ አመራር መከራ በዛባት እንጂ አልተረፈችም። ኢትዮጵያም ታሪኳም የሚቀጥሉት ሞትን በናቁ ጀግኖቿ እንጅ በሰርከስ ፖለቲከኞቿ አይደለም! እነርሱማ ሁሌም የመከራ ምንጯ ናቸው።
የሆነው ሆኖ ባንዳ ሲያፍር ይኖራል፤ ጀግና በተጋድሎው የዛሬንና የመጭውን ትውልድ አንገት ቀና ያደርጋል።
የሕዝብ ሥነ-ልቦናዊ ከፍታ ምንጩ ሞትን የናቁ ጀግኖች ናቸው!! እንደሆነብን ሁሉ ዛሬ እግራቸው ስር በወደቅን ነበር ምናልባት ሸብረክ ማለታችን የመስፈንጠሪያው አስገዳጅ ሁነት ስለሆነ ነው።
ከሕይወት በላይ ‘ክብር’ ዓላማ መሆኑን በተግባር መግለጥ በፎቶ ሲነበብ ሰውየውን ይመስላል!!
የታሪክ ሽሚያ ውስጥ የገቡ ‘የትንሽነት ኃይሎች’ ሐሰን ታንታዊ’ያቸውን ፈጥረዋል። እኛ ግን በተግባር ተፈትነው የማይሞት ታሪክ የሰሩ የሕዝብ ልጆችን የትውልዱ መማሪያ እናደርጋለን። እነርሱም ሆነ ጠላት ሰውየውን ያውቁታል። ገጽታው በራሱ ችግሮች ሁሉ ከሞት በታች ናቸው የሚል ሞትን የናቀ ወንድነቱን ይመሰክራል!! ሰውዬው ለጀግንነቱ ዕውቅናም ሆነ ሽልማቱ የሕዝብ ክብር ነው!!
ሕዝብ በፖለቲካ ሳይሆን በተግባር ያነግሣል! ታሪክ ይዘክራል! ፖለቲካ የሰቀለውን ጊዜ ይጥለዋል፤ ሕዝብ ያነገሠውን ግን ታሪክ አይጥለውም!
ወደር የሌለው የሕዝብ ልጅ
ብ/ጀኔራል ሻምበል በየነ – ባለከዘራው
©ሙሉአለም ገ.መድህን

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

“ውሳኔው እየመረረን የዋጥነው እውነታ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

Next Story

የቀድሞ የፓርላማ አባላት በመንግስት ከተሰጣቸው ቤት እንዲወጡ የተላለፈው ትዕዛዝ በፍርድ ቤት ታገደ

Go toTop