“ውሳኔው እየመረረን የዋጥነው እውነታ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

January 10, 2022

ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙ ሰዎችን ክስ በማቋረጥ ከእስር እንዲለቀቁ በመንግሥት በኩል የተደረሰው ውሳኔ ቁጣን የቀሰቀሰ መሆኑን እና መወሰድ የነበረበት እርምጃ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናገሩ።

ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ለአገራዊ መግባባት አመቺ ሁኔታን ለመፍጠር በሚል የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስና የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲዎች አመራሮችና አባለት እንዲሁም የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ክስ ተቋርጦ ከእስር እንዲወጡ መደረጉ ይታወሳል።

ይህንንም ተከትሎ የአንዳንዶቹን ከእስር መለቀቅ በተመለከተ ከተለያዩ ወገኖች ተቃውሞና ጥያቄ ሲቀርብ ተሰምቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት እሁድ አዲስ አበባ ውስጥ በተካሄደው አዲሱ የመከላከያ ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር በመንግሥት ውሳኔ ላይ የተሰማውን ተቃውሞ አንስተው ምላሽ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ጉዳይ “እኛንም መጀመሪያ ስንሰማው ያስደነገጠ ነው” በማለት፣ “ነገር ግን ቀኙን ስንፈትሽ ለኢትዮጵያ የሚበጅ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ጥቅም የሚያግዝ፣ የኢትዮጵያን ጠላቶች የሚቀንስ፣ በአውደ ውጊያ ያገኘነውን ድል በሰላሙ መድረክ እንድንደግም የሚያደርግ ነው” ሲሉ አስረድተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተሸነፉ ያሏቸው ኃይሎች “ክስ እንዲቋረጥ እና ከእስር ቤት እንዲወጡ ሲደረግ ከፍተኛ ቁጣ ቀስቅሷል” በማለት ይህም ቁጣ ከሁለት ወገኖች መሰንዘሩን ጠቅሰዋል።

አንደኛው ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም ሲኖር የማይደሰቱ ያሉት ሲሆን፣ “የት እንዳሉ የማይታወቁ . . . አጓጉል ብልጣብልጥነት የሚያጠቃቸውና እምብዛም ጆሯችንን የማንሰጣቸው” በማለት አጣጥለዋቸዋል።

ሁለተኛው ቡድን ደግሞ በዜናው ድንገተኝነት የደናገጠ “ለአገሩ ሁሉን ነገር ያበረከተ . . . ይህንን እኩይ ጠላት አምርሮ የሚጠላ እና ከዚህ ጠላት ጋር የሚደረግ ማንኛውም ንግግር ኢትዮጵያን ይጎዳል ብሎ የሚያምን ቅን ተቆጪ ነው” በማለት ይህንን ወገን መንግሥታቸው “ሙሉ በሙሉ ይረዳል፣ ያደምጣል፣ ለማስገንዘብም ጥረት ያደርጋል” ብለዋል።

BBC

“ኢትዮጵያ የጠቅላይ ሚኒስትሩ p.l.c አይደለችም”│ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ│ ክፍል 1│Sheger Times Media

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ፍትሕን እራሳቸዉ አልከሰከሷት!-መኮንን ብሩ(ዶ/ር)

Next Story

ወሬኛና አስመሳይ፣ ፈሪና አሻጥረኛ ፊልድ ማራሻል ወዘተ እየተባለ አንዳንዶች ሹመቶች ሲሰጣቸው አይተናል

Go toTop