መንገድ ሲመሩ የነበሩ የውስጥ ባንዳዎችን ወደ ሕግ ማቅረብ ተጀምሯል

December 20, 2021

አቶ ዘነበ ተክሌ የሸዋሮቢት ከተማ ምክትል ከንቲባ

የአሸባሪው ሕወሓት እና ኦነግ ሸኔ ሸዋሮቢትን ከተማ እንዲወሩና እንዲያወድሙ መንገድ ሲመሩ የነበሩ፣ መረጃ በመስጠት የተባበሩና በሰዎችና በንብረት ላይ ጉዳት እንዲደርስ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ የውስጥ ባንዳዎችን በመለየት ወደ ህግ ማቅረብ መጀመሩን የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ዘነበ ተክሌ በተለይም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለሻጹት፤ የአሸባሪው ሕወሓት ጁንታ ወራሪዎች ሸዋሮቢት ከተማ በገቡበት ወቅት ሁሉንም የግለሰብ ቤቶች አንኳኩተው ዘርፋ ማካሄዳቸውን፣ አዛውንቶች፣ ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ታዳጊዎች እና እናቶችን መድፈራቸውን ጠቁመው፤ በርካቶች ለከፋ የጤና እክል ተዳርገዋል።

ምክትል ከንቲባው እንደተናገሩትም፤ የአሸባሪው ሕወሓት ጁንታ ወራሪዎች ሸዋሮቢት ከተማን በወረሩበት ወቅት ሁሉንም የግለሰብ ቤት አንኳኩተው ዘርፋ የፈፀሙ ሲሆን የመንግሥትና ሌሎች ተቋማትን ለይተው ዘርፈዋል፤ የተቀረውን ደግሞ ሆን ብለው አውድመዋል። የአሸባሪው ኦነግ ሸኔ አባላት እና ቡድንም ከአሸባሪው ሕወሓት ጁንታ ጋር በመተባበር አስከፊ ተግባር ሲያከናውን እንደነበርም አረጋግጠዋል። አሸባሪዎቹ ነዋሪዎችን ገድለዋል፣ ንብረት ዘርፈዋል፤ አውድመዋል፤ ሴቶችን አስገድደው ደፍረዋል፣ የንግድ ተቋማትን አውድመዋል፤

(ኢ ፕ ድ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የአሸባሪው ህወሓት ኃይሎቹ ወደ ትግራይ እንዲመለሱ ማዘዙን ለተመድ በደብዳቤ ገለጸ

Next Story

አሸባሪው፣ የአማራ ቄስ ብልጽግና ነው በሚል ካህናቱን ማረዱን የደብረጸሐይ ሐሙሲት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርቲያን ካህናት ገለጹ

Go toTop