የቤተክርስቲያኒቱ አገልጋይ የሆኑት ዲያቆን ዳዊት መኮንን፣ መሪ ጌታ ተፈራ ጉባይ እና ቄስ ጌጤ ያለው በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢዎች እንደተናገሩት፤ መንግሥት በመንግሥትነቱ ያስተዳድራል፤ ገበሬውም ምርቱን ያመርታል። ቄሱም እንዲሁ በቅስናው በማገልገል ምዕመኑን ከክፉ እንዲመለስ ያደርጋል። ይህ ሳይሆን ቀርቶ ዛሬ ቀሳውስቱ በአደባባይ ይታረድ ይዟል። በስፍራው ለበርካታ ጊዜ ሲያሰቃያቸው የነበረው ግፈኛውና ወራሪው ቡድን፣ የቤተክርስቲያኒቱ አገልጋይ የሆኑት ቄስ ደጀኔ ወልዴና ቄስ ወዳጄ ጌታ ተገድለዋል።
ዲያቆን ዳዊት እንደተናገሩት ከሆነ፤ ወራሪው ጁንታ በቤተ ክርስቲያኒቱ ሞርታር የተባለውን መሳሪያ አጥምዶ እንዳትቀድሱ በማለት ሲያስፈራሯቸው ቆይተዋል። ይባስ በብሎም በቤተክርስቲያን ውስጥም ተጸዳድተዋል። ቅርሶችን አውድመዋል። የአማራ ቄስ በሙሉ ብልጽግና ነው በሚል ካህናትን.
….
(ኢ ፕ ድ)