በሸዋሮቢት ከተማ ለታሪክ ምስክርነት የተረፈ ንብረት የለም፤ ሙሉ በሙሉ ወድሟል

December 3, 2021
ህዳር 23 ቀን 2014 (ኢዜአ) መድሃኒት ቤቶች፣ ባንኮች፣ ሆቴሎች፣ ሱፐርማርኬቶች፣ የሸቀጣሸቀጥ ሱቆች፣ ተዘርፈዋል፤ ከዘረፋ የተረፉት ደግሞ ከጥቅም ውጭ እንዲሆኑ ተደርገው ወድመዋል።
የሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪዋ ወይዘሮ የውብዳር መሀመድ የሽብር ቡድኑ ከተላላኪው ሸኔ ጋር በመተባበር ከተማዋን አውድሟታል ይላሉ።
“ሐብትና ንብረት ይተካል” የሚሉት ወይዘሮዋ ወራሪው ንጹሃንን በአደባባይ በመረሸን የጭካኔውን ጥግ አሳይቷል ሲሉ ተናግረዋል።
የሽብር ቡድኑ ህወሓት ወራሪዎች መነኩሴ ሳይቀር በመድፈር ነውረኝነታቸውን አሳይተዋል ነው ያሉት።
“የትግራይ ወራሪዎች አንዲትን ሴት ስምንት ሆነው በመድፈር ለሰው ልጅ አዕምሮ የሚከብድ ኢ-ሠብዓዊ ድርጊት መፈጸማቸውን ተናግረዋል።
አሸባሪው ሃይል በጥቂት ቀናት ውስጥ ደብረ ሲናን እንዳልነበረች አድርጓታል። የጤና ተቋማቷን አፈራርሶ፣ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን ደረማምሶ ከፍተኛ ውድመት ፈጽሟል።
እናም እንላለን..
በመላው የአማራ ምድር ላይ ይሄን አይነት ጉዳት ያደረሰን አሸባሪ የገባበት ገብ*ተን የእጁን እንሰ*ጠዋለን እንጂ ከሸዋ ሸሽቶ ወደ አድዋ ስለሄደ ብቻ “አመለጠን” ብለን የምን*ተወው አይሆንም።
_ አካባቢህን ጠብቅ፣
_ ወደ ግንባር ዝመት፣
_ መከላከያን ደግፍ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር መመዘኛውን የሚያሟሉ ወጣቶችን ከህዳር 20/2014 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 15/2014 ዓ/ም ለመደበኛ ሠራዊት ወጣቶችን መመልመል ይፈልጋል፡

Next Story

የተበተነውን የጠላት ኀይል ትጥቅ ማስፈታት እና የዘረፈውን ለማስቀረት ሕዝቡ እንዲረባረብ የኢፌዴሪ ጦር ኀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጥሪ አቀረቡ

Go toTop